በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ 12 ሲሞቱ ሌሎች በፍርስራሹ ስር እንዳሉ ተሰግቷል


ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ 12 ሲሞቱ ሎሎች በፍርስራሹ ስር እንዳሉ ተሰግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:34 0:00

ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ 12 ሲሞቱ ሎሎች በፍርስራሹ ስር እንዳሉ ተሰግቷል

ፖሊስና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እስካሁን የደረሱበት ያልታወቀውን ሰዎች ለመታደግ ፍርስራሹን በማሰስ ላይ ናቸው። በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረባቸው 12 ሰዎች በኬንያታ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ ናቸው። የአደጋው መንስዔ ናይሮቢ ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ሲሆን በተለይ ደግሞ ለሕንፃው መፍረስ ምክንያት እንደሆነ የተነገረው አጠገቡ ያለ ወንዝ መሙላቱ ነው።

ፖሊስና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እስካሁን የደረሱበት ያልታወቀውን ሰዎች ለመታደግ ፍርስራሹን በማሰስ ላይ ናቸው።

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረባቸው 12 ሰዎች በኬንያታ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ ናቸው።

የአደጋው መንስዔ ናይሮቢ ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ሲሆን በተለይ ደግሞ ለሕንፃው መፍረስ ምክንያት እንደሆነ የተነገረው አጠገቡ ያለ ወንዝ መሙላቱ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ሰሞኑን ከተማይቱ ላይ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ የከተማዪን አውራ መንገዶችን በመዝጋት በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዋ ላይም ጫና አሳድሯል።

የፈረሰው ባለ ሰባት ፎቅ የመኖርያ ሕንፃ ሲሆን የሕንፃው የጥራት ደረጃ ዝቅተኛ መሆንም ለአደጋው ምክንያት ነው ተብሏል።

የናይሮቢ አስተዳደርም ይህ አደጋ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ከደረሰ በኋላ ከተማዪቱ ውስጥ ባሉ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስቧል።

ደረጃዎችን የማይመጥኑ የመኖርያ ሕንፃዎችን በንብረትነት የያዙ ባለሀብቶችንም ሕግ ፊት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።

የናይሮቢ ከተማ ገዥ ኢቫንስ ኪዴሮ በአደጋው ቦታ ተገኝተው እየተካሄደ ያለውን የነፍስ አድን ሥራ ከተመለከቱ ባኋላ ባደረጉት ንግግር ሕንፃው በተደረመሰበት አካባቢ የሚኖሩትን ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ እንደሚያዛዉሯቸው አሳውቀዋል።

ባለፈው ዓመት ጥር ውስጥም የአሁኑ አደጋ በደረሰበት አካባቢ የነበረ ባለ ስድስት ፎቅ የመኖርያ ሕንፃ ተደርምሶ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን በወቅቱ የናይሮቢ ከተማ አስተዳደር የሕንጻውን ባለቤት ሕግ ፊት ለማቅረብ ቢጥርም ሙስናና ሌሎች እንቅፋቶች ግለሰቡን እንዳንፋረድአድርጎናል ሲሉ የከተማዪቱ ገዥ ሚስተር ካዴሮ ብሦት አሰምተዋል።

"ባለሃብቶች ወንዝ ዳርም ላይ ሕንፃ እንዲገነቡ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። እኛ በወንዝ ዳር ላይ ሊገነባ ያለውን ግንባታ ለማስቆም ስንሞክርይቀድሙህና ፍርድ ቤት ሄደው ፍቃዳቸውን ያስለቅቃሉ፡፡ ይሄ አንዱ ምክንያት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ሙስና ነው። አሁን ግን በሚወሰደው እርምጃ ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚመጣ ዋጋውን ያገኛል።" ብለዋል።

ከትናንት በስተያ ቅዳሜም የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ቦታውን በጎበኙበት ወቅት የሕንፃው ባለቤት በፍጥነት በቁጥጥር ሥርእንዲውል አዝዘው የነበሩ ሲሆን ሳሙዔል ካማው የሚባሉ ተፈላጊው ባለሀብት እርሳቸው በሚያዙት ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው እጅ መስጠታቸውን በናይሮቢ የእስታሬሄ አካባቢ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኦፊሰር ዓሊስ ኪሜሊ አስታውቀዋል።

የኬንያ ሚቲኦሮሎጂ መሥሪያ ቤት እንደሚለው ዝናቡ በዋና ከተማዪቱ ናይሮቢና በአካባቢዋ መጣሉን ይቀጥላል።

ኬንያ ውስጥ በደረሰ የህንጻ መፍረስ 12 ሲሞቱ ሌሎች በፍርስራሹ ስር እንዳሉ ተሰግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG