በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኦሮሚያ ወደ ሞያሌ የሚሄዱ ሰዎች በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ እሥራትና እንግልት እየደረሰብን ነዉ ይላሉ


ኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ ሞያሌ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/
ኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ ሞያሌ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/

የአሜርካ ድምጽ ታሠሩ የተባሉትን ወጣቶች ጉዳይ አስመልክቶ፥ የአካባቢዉን የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ቢጠይቅም፥ ሃላፊዎቹ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተለያዩ ከኦሮምያ አካባቢዎች ወደ ሞያሌ የሚሄዱ ሰዎች፥ የፖሊስ ኃይል ያለ ምንም በቂ ምክኒያት ይዞ እያሰረን ነዉ በማለት ተናገሩ። ብዙዎቹ የጉልበት ስራ ፍለጋ ሌሎች ደግሞ ለግል ጉዳያቸዉ ወደ ሞያሌ የመጡ ናቸዉ። የሞያሌ ከተማን በከፊል የሚያስተዳድረው የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ነው እየያዘ የሚያስራቸው ተብሏል። ከእነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ እስከ ሁለት ወር በእስር እንደሚያቆያቸዉ ይናገራሉ። ከምዕራብ ሸዋ የጉልበት ሥራ ፍለጋ ወደ ሞያሌ መጣሁ ያለ አንድ ወጣት፥ ከተማዋ በገባበት ማግሥት የመታወቂያ ወረቀት ለጠየቁት ፖሊሶች ቢያሳይም፥ ያለ ምንም ምክኒያት ለ 2 ወር እንዳሠሩትና ወንጀል እንዳልሠራ ያስረዳል።

ኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ ሞያሌ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/
ኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ ሞያሌ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/

”ሁለት ሆነን ስንሄድ ነበር። አብሮኝ የነበረዉን ልጅም እንደ ያዙት። ከዚያ ብሄራችንን ጠየቁን። ኦሮሞዎች ነን ብለን ስንነግራቸዉ እናንተ ሽፍቶች ናችሁ አሉን። ቀጥለው ስልካችንን ፈትሸው የኦሮምኛ ዘፈን አገኙ። በቃ ከዚያ ቦኋላ ወደ እሥር ቤት ወሰዱን። እሥር ቤታቸዉ ምንም ምግብ የሚባል ነገር የለዉም። ሰዎች ካዘኑልን በ 2 አልያም በ3 ቀን አንዴ ከሆቴል ትርፍራፊ ምግብ ያመጡልናል እንጂ ምንም ነገር የለም። በጣም ነዉ ሲጎዱን የነበረዉ። ሲለቁኝም ለፍርድ ቤት አላቀረቡኝም። ጉቦ ወስደዉ ነዉ የለቀቁኝ፣ ደግሞስለቀቅም ይህን አጥፍተሃል ተብሎ የተነገረኝ ምንም ነገር የለም።” ብለዋል።

ሌላዉ ከምዕራብ አርሲ ዞን ከጓደኛዉ ጋር ወደ ሞያሌ ስልክ ለመግዛት መጥተን እንዲሁ ተያዝን የሚል አንድ የኮሌጅ ተማሪ፥ አሁንም በሞያሌ ከተማ ቁጠባ በሚባል አካባቢ ከሌሎች ከኦሮሚያ ዞኖች ወደ ከተማዋ የመጡ ወጣቶች ታስረው እንዳሉ ይናገራል።

”አብረን ከጓደኛዬ ጋር ተይዘን ስንሄድ፥ እስር ቤቱ ዉስጥ ሥራ ፍለጋ የሄዱ፣ ሌሎች የታሰሩ ሰዎች አገኘን። ሌሎች ደግሞ ልክ እንደኛው የሚያስፈልጋቸዉን ነገር ለመግዛትወደ ከተማዋ ሲገቡ የተያዙ ናቸዉ። ነገር ግን ከሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ልጆች ይበዛሉ።” ብለዋል።

ኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ ሞያሌ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/
ኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ ሞያሌ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/

ወጣቱ አክሎ ሲናገርም፥ ከ 15 ቀናት በላይ ከታሰርኩ በኋላ ጉቦ ሰጥቼ መዉጣት ችያለሁ ብሏል። ነገር ግን በስሙ ፈይሳ ያዳ የሚባለዉ አብሮት የተያዘዉ ጓደኛዉ የእጅ ስልኩ ዉስጥ የኦሮምኛ ዘፈን በመገኘቱ እስካሁን እንደታሠረ መሆኑን ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ታስረዋል የሚባልበት ሥፍራ የፖሊስ ጣብያ እዳልሆነና ሰዎች እንኳን ለመጠየቅ ቢፈልጉ ጠባቂዎች እንደማያስገቧቸዉ እነዚሁ ታስረው የወጡ ወጣቶች ይናገራሉ።

ይህ ሁኔታ እየተፈጸመ ነዉ ወደ ተባለዉ በሶማሌ ክልል የሞያሌ ፖሊስ ጽህፈት ቤትም ሆነ በአቅራብያዉ የሚገኘዉን ፍርድ ቤት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ሙከራ ብናደርግም ልናገኛቸዉ አልቻልንም። የኦሮሚያ ክልልም የከተማዋን 01 ቀበሌ የሚያስተዳድር ሲሆን ስለ ጉዳዩ የሚያዉቁትን ነገር ብንጠይቃቸዉም ሃሳብ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም በማለት መልስ ሰጥዋል።

ከኦሮሚያ ወደ ሞያሌ የሚሄዱ ሰዎች በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ እሥራትና እንግልት እየደረሰብን ነዉ ይላሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG