ኬንያ ቁጥራቸዉ 25 የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋ ሰጠች ፣ በተጨማሪም 41 የምሆኑ ሌሎች ጥገኝነት ፍለጋ ወደ ኬንያ የሸሹ የኢትዮጵያ ዜጎችም በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር አውላለች ሲሉ የኦሮሞ ህበረሰብ መሪ አቶ ሸጋ አረዶ ለቪኦኤ ገልጸዋል።
በኬንያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ቃል አቀባይም ተባረሩ ሰለተባሉት 25 ጥገኝነት ጠያቂዎች ሁኔታ ለማጣራት ቃል ገብቷል።
በመጀመርያ ዓርብ ዕለት ወደ 12 የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ከነዚያም 13ቱ ደግሞ በትላንትዉ ዕለት ነበር ኬንያ በሞያሌ ላለዉ የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ እንደተላለፉ የተነገረዉ። አቶ ሸጋ አረዶ በናይሮቢ የኦሮሞ ማህበረሰብ መሪ ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ አርብ እለት 12 ትላንት ደግሞ 2 ሰደተኞች ኢትዮጵያን ከሚያዋስነዉ የኬንያ ከተማ ሞያሌ የተባረሩ ሲሆን 10ሩ ደግሞ አርብ እለት ከደቡባዊ የኬንያ ከተማ ከሜሩ ለኢትዮጵያ መንግስት ተሰጥተዋል። የኬንያ መንግስት የጥገኝነት ጠያቂዎቹን ችግር ሳያጣራ ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ መስጠቱ እጅግ አሳሳቢ ነዉ ብለዋል አቶ ሸጋ።
“አንድ ሰዉ ወደ ኬንያ ድምበር ከተሻገረ የኬንያ እሚግሬሽን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለኢትዮጵያ እሚግሬሽን በማስረከብ ላይ ነዉ” ይላሉ አቶ ሸጋ።
አክለውልም፣ “ለምሳሌ ከትላንትና ወድያ ወደ 12 የምሆኑ ተማሪዎችን ለ እትዮጵያ እምግሬሽን አሳልፎ ሰጥቶዋል። በትላንትናዉ ዕለት በሜሩ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበሩት 10 እትዮጵያዉያንም በግድ ወደ እትዮጵያ እንድመለሱ ተወስኖ በሞያሌ ለምገኘዉ ለእትዮጵያ እምግሬሽን ቅርንጫፍ ተሰጥተዋል። በተጨማሪም 3 የምሆኑ በትላትናዉ ዕለት በተመሳሳይ ሁኔታ እንድመለሱ ወደ ኢንዲመለሱ ተገደዋል” ብለዋል።
“አሁን እየሆነ ያለዉ ጥገኝነት ፍለጋ ወደ ኬንያ የምመጣዉን ሰዉ መልሶ በማስረከብ ነዉ። ስለዚህ (UNHCR) እና የኬንያ መንግስት፡ በተለይም የኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሁኔታዎችን አመቻችቶ እነኚህን ሰዎች ሊታደግ ይገባል እንጂ ማንም በኦሮሞ ስደተኖች ላይ እንደፈለገ እንድሆን አንፈቅድም። ስለዚህ እንደ አንድ ማህበረሰብ ለምመለከተዉ አካል አቤት እንላለን።”
በተጨማሪም አቶ ሸጋ በአሁኑ ግዜም 41 የምሆኑ የኦሮሞ ስደተኞች በማርሳቢት በፖለስ ቁጥጥር መዋላቸዉን ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅች (UNHCR) የኬንያ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዱክ ምዋንጫ (Duke Mwancha) በኬንያ መንግስት ለኢትዮጵያ ተሰጡ ስለተባሉ ጥገኝነት ፈላጊዎች መስሪያ ቤታቸዉ እንደሚያጣራ ገልጸዉልናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ባለፈዉ ቅዳሜ ጠዋት ወደ 100 የምሆኑ የኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች ሁለት ኬንያዉያንን አግተዉ መዉሰዳቸዉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቦዋል። የኬንያው ዴይሊ ኔሽን (Daily Nation) እና ስታንዳርድ (The Standard) ጋዜጦች በቅዳሜ ዕትማቸዉ እንዳስነበቡት የኢትዮጵያ የጸጥታ ኅይሎች ከማርሳቢት ከቦሪ ቀበሌ ማህበር ዉስጥ 2 ሲቪሎችንና መሳርያም ወስደዉ ሄደዋል በማለት ዘግበዋል።
የማርሳቢት ግዛት ኮምሽነር ሞፋት ካንጊ ለኬንያው ደይሊ ኔሽን ጋዘጣ እንደተናገሩት፣ ጥቃቱን ለምን እንዳደረሱ ምክንያቱን ለግዜዉ ባናዉቅም ሰዎቹ ግን የኢትዮጵያ ጸጥታ አባል መሆናቸዉን ደርሰንበታል ብለዋል።
ኮምሽነሩም ጨምረዉ ሰዎቹ 2 ሰዎችንና 2 የጦር መሳርያዎችንም ወስደዋል ሲሉ የሁኔታዉን ዝርዝር አስረድተዋል። የኬንያ መንግስት ስለጉዳዩ በይፋ የተናገረ ነገር ባይኖርም ኮምሽነር ካንጊ ግን ጉዳዩን በዲፕሎማስያዊ መንገድ የምንሄድበት ይሆናል ብሎዋል።
የእትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በዚህ ባሳለፈነዉ ዓመት መጨረሻ ወደ ኬንያ ድምበር ጥሰው በመግባት 3 የኬንያ ፖሊሶችን መግደላቸዉንም የኬንያዉ ዴይሊ ኔሽን (Daily Nation) ጋዜጣ ዘግቧል። የጸጥታ ሃይሎቹ የኬንያ ድንበር ላይ ወሰዱ ሰለተባለዉ እርምጃም ሆነ ጥገኝነት ጥያቄ የኦሮሞ ስደተኞችን ወኪል መንግስት ሰለመቀበሉ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የሰጠዉ አስተያየት የለም።
ዳዊት ገልሞ ከናይሮቢ የላከውን ዘገባ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።