በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ያሉ ኦሮሞ ጥገኝነት ጠያቂዎች መብት እንዲከበር የመንግሥታቱ ድርጅት ጠየቀ


አንድ ሴት በኬንያው ዳጋሃሌ ዳዳብ የስደተኞች ሠፈር በሚገኘው የተባባሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር ቢሮ ውስጥ[ ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS]ፋይል/
አንድ ሴት በኬንያው ዳጋሃሌ ዳዳብ የስደተኞች ሠፈር በሚገኘው የተባባሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር ቢሮ ውስጥ[ ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS]ፋይል/

ሰሜን ኬንያ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉት ጥገኝነት ፈላጊ የኢትዮጵያ ዜጎች መብታቸው እንዲከበር ኬንያ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቅርንጫፍ ጠየቀ።

ጉዳያቸው ዛሬ ፍርድ ቤት ሊቀርብ የነበረውን 28 ጥገኝነት ጠያቂ ኦሮሞዎችን ጉዳይ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር የኬንያ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ጣልቃ በመግባት ጉዳያቸው በጥልቀት እንዲታይ እና ለአንድ ሣምንት እንዲራዘም መጠየቁን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዱክ ምዋንቻ ለአሜሪካ ድምጽተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኬንያ 25 ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ ሰጥታለች የሚለውንም ዜና የኬንያ መንግሥት አስተባብሏል።

ዩኤንኤችሲአር ባወጣው መግለጫ፣ ቁጥራቸዉ 28 የሚደርስ የኦሮሞ ተማሪዎች በሰሜን ኬንያ ማርሳቢት አካባቢ ታስረዉ እንደሚገኙ ገልጿል።

ዳዳብ በሰሜን ኬንያ የሚገኝ ከዓለም ትልቁ የስደተኞች ካምፕ ነው
ዳዳብ በሰሜን ኬንያ የሚገኝ ከዓለም ትልቁ የስደተኞች ካምፕ ነው

ተማሪዎቹ ወደ ኬንያ ተሰደዉ ጥገኝነት ለመጠየቅ ሲጠባበቁ የኬንያ ፖሊስ ወደ ኢትዮጵያ መልሶ ለማባረር ቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸዉ ታውቋል። በዚህም መሰረት የዓለም አቀፋ የስደተኞች ድርጅት ኬንያ ቅርንጫፍ ጣልቃ ገብቶ ጉዳያቸዉን ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ሳምንት ጊዜ እንዲሰጠዉ የኬንያን መንግስት መጠየቁን ቃል አቀባዩ ዱክ ምዋንቻ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

“ይህንን ጉዳይ ለሳምንት እንዲቆይ ጠይቀናል። ምክንያቱም ጉዳዩን በጥልቀት እንድናይ፣ የህግ ባለሞያዎቻችንም ለጥገኝነት ፈላጊዎቹ እንድንልክ ግዜ ለማግኘት ነዉ” ብለዋል።

አክለውም፣ “ስደተኞችን በእንደዚህ አይነት ቦታ ተክተዉ ለመብታቸዉ የሚቆሞም የስደተኞች አካል በኬንያ ወይም እንደ(Refugee Consortium of Kenya) በመባል የሚታወቁ ድርጅቶችን ወደ ቦታዉ እንልካለን” በማለት መልስ ለቪኦኤ ሰጥተዋል።

ባለፈዉ ሳምንት ኬንያ ስደተኞችን ለኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን አሳልፋ ሰጠች የተባለዉንም ጉዳይ ለኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ (Department of Refugee Affairs/DRA) አቅርበን የናይቢሮዉ ቃል አቀባይ ስታንሊ ኛሌ ስለ ጉዳዩ ለጊዜዉ አስታያየት መስጠት አልችልም ብለዋል። ነገር ግን ቢሮዉ ናይሮቢ ላለዉ የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ኬንያ ስደተኞችን አልመለሰችም በማለት አስተባብለዋል ።

"ለመንግስት ባለስልጣናት ስለዚህ ሁኔታ አንስተንላቸዉ ነበር ነገር ግን አስተባብለዋል። እኛ ደግሞ የምንመሰረተዉ ከመንግስት በምናገኘዉ መረጃ ነዉ በቂ መሳርያ በሁሉም የሃገሪቱ ቦታዎች ስላላቸዉ። ይህንን ጉዳይ በትክክል 'ይህ ነዉ' ማለት ባንችልም እዉነቱ ጋር ለመድረስ በራሳችን በኩል ጥናት እያደረግን ነው። ከመንግስት ያገኘነው መረጃ ግን ይህ ነገር በርግጥ አለመከሰቱን ነዉ። በአሁኑ ግዜ በእጃችን ያለዉ መረጃ በማርሳቢት አካባቢ ታስረዉ ስላሉት 28 የኦሮሞ ወጣቶች ነዉ። የእነርሱንም ጉዳይ ለመከታተል የአንድ ሳምንት ጊዜ ጠይቀናል" ብለዋል።

በቁጥጥር ይገኛሉ ስለተባሉ የኦሮሞ ስደተኞች ለናይሮቢዉ ኦሮሞ ማህበረሰብ መሪ ለአቶ ሸጋ አረዶ ዳግም አንስተን እስካሁን የጥገኝነት ጠያቂዎችን ማንነትም ሆነ ያሉበትን ሁኔታ ምንም አናዉቅም ብለዋል። በፊት ተያዙ የተባሉት 41 ጥገኝነት ፈላጊዎች አሁን 28 ብቻ ናቸዉ የተገኙት ብለን ስንጠይቃቸዉ በአካባቢዉ በቂ ለሰብአዊ መብት የሚቆሙ ድርጅቶች ባለመኖራቸዉ እንደሌሎቹ ሊመልሷቸዉ ይችላሉ በማለት ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በተጨማሪም አቶ ሸጋ በማርሳቢት አካባቢ በተለይ በኦሮሞ ጥገኝነት ፈላጊዎች ላይ እየደረሰ ነዉ ያሉትን የሰባዓዊ መብት ረገጣ የዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መፍትሔ እንዲፈልጉ ተማጽነዋል።

ለአሜርካ ድምጽ ገልሞ ዳዊት ከናይሮቢ አጠንናቅሮ የላከውን ዘገባ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በኬንያ 28 የኦሮሞ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መብት እንዲከበር ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:54 0:00

XS
SM
MD
LG