በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሚያ አርብቶ አደሮች ማኅበር የ2016 የኢክዌተር ሽልማት አሸናፊ ሆነ


በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ማኅበርን ለአካባቢ ጥበቃና ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ አበርክታችኋል በማለት በስሙ (EQUATOR AWARD) የተሰኘዉን ሽልማት በናይሮቢ ሸለማቸዉ። UNDPን ወክለዉ ሽልማቱን ለማህበሩ መሪ ያበረከቱት ማይክል ባሊማ ማኅበሩ ቀጣይነት ላለዉ ዕድገትና ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተዉን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

የኦሮሚያ አርብቶ አደሮች ማህበር የ2016 የኢክዌተር ሽልማት(Equator Award) አሸናፊ ሆነ። ማህበሩ ይንን ሽልማት ያገኘዉ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም UNDP ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ በአካባቢ ጥበቃ ና ቀጣይነት ያለዉን ዕድገት ለአርብቶ አደሮች በማበርከቱ ነዉ ተብለዋል። ከተባበሩት መንግስታት የልማትፕሮግራም ሽልማቱን የተቀበሉት የማህበሩ መሪ ዶክተር አብዱላሂ ሓጅ በጊዜዉ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱን ማሸነፍ የቻልነዉ የኦሮሞ ባህል ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት ስለሚሰጥ ነዉ ብሎዋል። ማህበሩ ሽልማቱን ማሸነፉ የተነገረዉ በፓሪሱ የከባቢ አየር ለዉጥ ጉባኤ ላይ ሲሆን ሽልማቱ ዛሬ የተሰጠዉ እአአ ከ1970 ጀምሮ ሲከበር የቆየዉን ባለፈው አርብ የተከበረውን "World Earth Day" ምክንያት በማድረግ ነዉ።

የኢክዌተር ሽልማት​ በአካባቢ ጥበቃና ቀጣይነት ያለዉን ዕድገት ላበረከቱ ማኅበራት የሚሰጥ ልዩ ሽልማት ሲሆን የኦሮሚያ አርብቶ አደሮች ማኅበርም በ4 የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ማለትም በኬንያ፣ በኢትዮጵያ፣ በጂቡቲ ና በታንዛንያ ዉስጥ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ብዙ የአካባቢ ጥበቃ ሥራን በመሥራቱ ሽልማቱን ማሸነፍ ችለዋል።

በኬንያ መዲና ናይሮቢ ሽልማቱን ለማህበሩ የሰጡት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ማይክል ባሊማ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ማህበርን ሥራ አመስግነዋል።

"መጀመርያ ይንን ሽልማት ያዘጋጁትን አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ። በመቀጠልም ይንን ሽልማትያሸነፉት የኦሮሚያ አርብቶአደሮች ማህበር አንድ ህዝብ መሬቱ ላይ በሙሉ መብት መሬቱንና ያለዉን ሃብቱን በተገቢ ሁኔታ ሲያስተዳድር ለአካባቢ ጥበቃና ቀጣይነት ላለዉ ዕድገት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ በተግባር አሳይታቹናል።" ብለዋል።

ባሊማ ጨምሮው ሲናገሩ በተለይ በሰሜን ኬንያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉ አርብቶ አደሮችን ለመደገፍ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ከ12 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል። ተጨማሪ ዝርዝሩን ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የኦሮሚያ አርብቶ አደሮች ማኅበር የ2016 የኢክዌተር ሽልማት አሸናፊ ሆነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG