በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሃዋሳው ግጭት የተጠረጠሩ ታሰሩ


በሃዋሳ ከተማ ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ግጭት እጃቸው አለ ያላቸውን 37 ሰዎችን ማሰሩን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር 18 ሲቪሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሞተ ሰው አለመኖሩን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

ከተማው ሰላማዊ እንዳይሆንና ለግል ጥቅም ሲባል ከተማዋን የሚያሸብር ቡድን አለ ያለው የከተማው ፖሊስ በምርመራ ሲረጋገጥ ይገለፃል ብሏል፡፡

ቅዳሜና እሁድ እንዲደረጉ መርሃግብር የተቆረጠላቸው ሁለት ጨዋታዎች ለከተማው ሰላምና ፀጥታ ሲባል መሰረዙን የከተማው ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ገልጿል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በሃዋሳው ግጭት የተጠረጠሩ ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG