በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ


የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከአምስት ሺህ በላይ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከመቱ ሁለተኛ ሳምንት መያዙን ተናገሩ፡፡

ሰራተኞቹ ሥራ አቆምን ያሉት በሚደረስባቸው የአስተዳደር በደል ፣ ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዙ ችግሮች ሲሆን በደል አድርሰውብናል ያሏቸው ስድስት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች እንዲባረሩ ይጠይቃሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጥያቄቸው ተገቢ ባይሆንም ከምግባቸው ላይ የሚቀነሰውን ገቢ ግብር ሳሊኒ ኩባኒያ እንዲሸፍን ፤ በደመወዛቸው ላይ ደግሞ 450 ብር እንዲጨመር ተማምነናል ብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ መቀጠል ስላለበት ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች እንደሚሰናበቱ ተወስኗልም ተብሏል፡፡

በህግና በማስረጃ እንጂ የደቦ ፍትህ በመፈለግ ስድስት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ይባረሩ ማለታቸው ስህተት ነው ብሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG