ሀዋሳ —
ሰብዓዊ ድጋፍ ተቋርጦ እንደነበረ የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀው በአካባቢው አሁንም የፀጥታ ችግር ስላለ ተፈናቃዮቹን ወደየቀያቸው ለመመለስ መቸገራቸውን አመልክተዋል።
ተፈናቃዮቹ በቂ ድጋፍ እንደማይደረግላቸውና እስከ አሁን በምግብ እጥረት ሰባት ህፃናት መሞታቸውን አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት የተቆራረጠ መሆኑን ያሳወቀው የደቡብ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር “ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ የማድረግና ወደየቀያቸው መመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው” ብሏል።
ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ