ሀዋሳ —
በሀዋሳ ከተማና ሲዳማ ዞን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተዘግተው ዋሉ፡፡
መስሪያ ቤቶቹ ተዘግተው የዋሉት "ኤጄቶ" በመባል የሚጠራው የሲዳማ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ ለሦስት ቀናት ሥራ የማቆም አዱማ ማወጃቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ወጣቶች ዛሬ ጠዋት በስራ ገበታቸው የተገኙ ወጣቶች ቢሮአቸውን ለቅቀው እንድወጡና እንዲዘጉ እንዳስገደዷቸው ለቪኦኤ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡
ሥራ የማስቆም አዱማ ዓላማው የሲዳማን ጥያቄ ለመቀልበስ የሚደረገውን ጥረት የሚቃወም አዱማ መሆኑን የሚናገረው የሲዳማ መብትና ነፃነት ተሟጋችና አክቲቪስት ታሪኩ ለማ ከሰላማዊና ከህግ አግባብ ወጭ የሚሆኑ ነገሮችን የኤጄቶ ትግል አቅጣጫ ለማሳት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው ብሏል፡፡
የመንግሥት አካላት በዚህ ዙርያ ሀሳብ እንዲሰጡ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ