ሀዋሳ —
አጣዳፊ ተቅማጥና ማጅራት ገትርን የመሳሰሉ ወረርሽኝ አስከታይ ችግሮች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ መታየታቸውን እዚያው ያሉ የአከባቢው የጤና ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡
በመጠለያ ጣቢያዎች ተከሰቱ ባሏቸው ሕመሞች የሞቱ ሰዎች መኖራቸውንም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።
"ዓለምአቀፉ “ድንበር የለሽ ሃኪሞች" ቡድን በምህፃሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ ከፍተኛ የምግብ እጥረት መኖሩን ገልፆ ዜጎች ለከፋ ወረርሽኝ ለጋለጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡
ቡድኑ የተፈናቀሉ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ጠቅሶ ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች እንዲረባረቡና እርዳታቸውን እንድያሳድጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ለቪኦኤ በሰጠው መግለጫ “ወረርሽኝ ተከስቷል” መባሉን አስተባብሎ ታምመው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ተመርምረው ከተጠቀሱት በሽታዎች “ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል” ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ