ደቡብ ክልል —
ሲቪሎችን የገደሉ፣ ያፈናቀሉና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦችን መንግሥት ይዞ ሕግ ፊት እንዲያቀርብም ጠይቀዋል።
በሺሆች የሚቆጠሩ የጌዴዖ ብሔረሰብ አባላት አሁንም ችግር ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ለ364 ሺህ ሰው ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የጌዴዖ ዞን አስተዳዳሪ አሳስበዋል።
የብሄራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተፈናቃዮችን ከበልግ እርሻ ወቅት በፊት ወደየቀያቸው ለመመለስ የሚያስችል ጥረት እያደረገ መሆኑንና ዲላ ከተማ ላይም ማዕከል ማቋቋሙን ገልጿል።
(ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ