በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ጥቅምት 2/2012 ዓ.ም ከለሊቱ ዐስር ሰዓት አከባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የልዩ ወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ነው የሚባለው «ብሄር ተኮር ፌዴራሊዝም» ብሄርና ብሄረሰቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰንና በቋንቋቸው የመጠቀምና የመዳኘት መብት ሰጥቷል ቢባልም ለአንድነት መሸሸርና መከፋፈል ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ለማስፈፀም የሚረዳ የህግ ሰነድና የአሰራር ማዕቀፎችን እያዘጋጀ መሆኑን የውሳኔ ህዝብ ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት አስታውቀ።
ዴሞክራሲ በተግባር
የሚነሱ ቅሬታዎች ሚዛናዊነትን፥ የጋራ እሴቶቻችንንና መርኆችን በጠበቀ መንገድ መቅረብ አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መክረዋል።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ዙሪያ ከቤተክርስቲያንቷ ጋር በሃዋሳ ከተማ መከሩ።
በደቡብ ክልል የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ በአካባቢው የነገሰው የፖለቲካ ውጥረት ለክልሉ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ቀውስ መንስዔ መሆኑ ይታመናል።
ከመልካም ወጣት ፕሮጀክት መሪ ዮናታን አክሊሉ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ክፍል ሁለት)
አዲሱ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ማን ናቸው? የት ምን ሰርተዋል? የደቡብ ኢትዮጵያ ሀዝቦቸ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን ማዕከላዊ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገሰ ባልቻ የሚከተለውን ስለእርሳቸው ብለዋል፡፡
ባለፉት 28 ዓመታት ለደቡብ ክልል ከሲዳማ ውጭ የሌላ ብሄር ተወላጅ በርዕሰ-መስተዳደርነት ሲሾም አቶ ርስቱ ይርዳው ከአቶ ኃይለማርያም ቀጥሎ ሁለተኛ ሰው ሆነዋል።
ከመልካም ወጣት ፕሮጀክት መሪ ዮናታን አክሊሉ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ክፍል አንድ)
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች ሰዎች ከቀያቸው፣ ከተወለዱበትና ጎጆአቸውን ቀልሰው ከሚኖሩበት ስፍራ ሲፈናቀሉ ኑሮአቸውም አብሮ ምስቅልቅሉ ይወጣል።
በከባድ የሥነ-ምግባር ግድፈት ከአመራር አባልነትና ከድርጅቱ የተሰናበቱ ግለሰቦች የሲዳማን ህዝብ ጥያቄ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ ነው ሲል በአቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመራው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከስሷል።
ህጋዊው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ በኛ የሚመራው ነው» የሚለው የነዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶ ቡድን ዛሬ በጠራው የማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ለመጭው ብሄራዊ ምርጫ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
በሀዋሳ ከተማና ሲዳማ ዞን ሐምሌ 11 በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ፤ በተለምዶ "የኤጄቶ መሪዎች" የሚባሉ ግለሰቦች እያንዳንዳችው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንድለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰኔ አስተላለፈ፡፡
1440ኛው የኢድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሀዋሳ
በሃዋሳ ከተማ አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችና የሰዎች ማንንት ላይ ያተኮሩ ትንኮሳዎች ነዋሪው ተርጋግቶ እንዳይኖርና ስጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሃዋሳ፣ በሲዳማ ዞን ወረዳዎች አና በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የተሰቀሉ ሕጋዊ ያልሆኑና የማን እንደሆኑ የማይታወቁ አርማዎች ፣ ምልክቶች እና ባንድራዎች ወርደው በሁለት ቀናት ውስጥ በክልሉ ሕጋዊ ሰንደቅ አላማና አርማዎች እንዲተኩ የክልሉ ጊዜያዊ ወታደራዊ እዝ ትእዛዝ ሰጠ፡፡
ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብረዋል።
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “በሀገሪቱም ሆነ በክልል የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እየጎለበተ መሄዱን” ጠቅሶ በተቃራኒው ግን “የለውጥ ተፃራሪዎችና የለውጡን ሂደት በአግባቡ ያልተረዱ” ያላቸው “ሁከትና ብጥብጥ በክልሉ አስነስተዋል” ሲል ከስሷል።
ተጨማሪ ይጫኑ