በሀዋሳ ከተማና በክልሉ ተፈጥሮ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ደኢህዴን ) የስራ ሃላፊዎችን ማገዱን አስታወቀ።
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “በሀገሪቱም ሆነ በክልል የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እየጎለበተ መሄዱን” ጠቅሶ በተቃራኒው ግን “የለውጥ ተፃራሪዎችና የለውጡን ሂደት በአግባቡ ያልተረዱ” ያላቸው “ሁከትና ብጥብጥ በክልሉ አስነስተዋል” ሲል ከስሷል።
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በመሪዎቹ ጥያቄ መሠረት በወታደራዊ ዕዝ ሥር መዋሉ ተገለፀ፡፡
የሲዳማን ክልል እንሁን ጥያቄ ተከትሎ በዞኑ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሁከት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በክልል የመደራጀት ጥያቄዎች የደቡብ ኢትዮዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በ10ኛው ጉባኤ በጥናትና በህግ አግባብ እንደሚፈታ ባስቀመጠው ውሳኔ መሰረት ምላሽ እንደሚያገኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ላለፉት 10 ተከታታይ ቀናት ባካሄደዉ ስብሰባ ሀገራዊ የስላምና ፀጥታ ሁኔታን ከአህጉራዊና ዓለምቀፋዊ ሁኔታ ጋር አገንዝቦ መገምገሙን አስታወቋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 28/2011 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡
የወላይታ ህዝብ ክልል የመመስረት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ በአስቸኳይ ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ /ወብን/ እና የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ወህዴግ/ አሳሰቡ፡፡
የውሳኔ ህዝብ የሚካሄድበት ቀን የጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት በሚቀጥሉት አምስት ቀናት ቀን ተቆርጦ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በሲዳማ ስም የተደራጁ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አሳሰቡ፡፡
መልሶ ለማቋቋምና ለዘላቂ ልማት የሚውል ከዴንማርክ፣ ከጃፓንና ከተባበሩት መንግሥታት የልማት መርኃግብር - ዩኤንዲፒ በተገኘ አምስት ሚሊየን ዶላር 5 ሺህ ሰዎች በመጀመሪያ ዙር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የመርኃግብሩ የኢትዮጵያ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ በመምህራንና ሰራተኞች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሥራ አቁሟል፡፡
"የዱራሜ ከተማ መስጅድ ተቃጥሏል፣ ኢማሙም ተገድሏል" በሚል በአሉባልታ ወሬ በደቡብ ክልል ሃላባ ቁልቶ ከተማ በእስልምና እምነት ተከታዮችና በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭትና ተቃርኖ በዕርቅ ተፈታ፡፡
በምዕራብ ጉጂና በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች ለሦስት ዓመታት የዘለቀው ግጭትና ጥቃት ትናንት በወረደ ዕርቀ ሰላም እልባት ተበጅቶለታል ተብሏል፡፡
በደቡብ ክልል ከተሞች የህዝቦችን አንድነትና ግንኙነት ያጠናክራሉ የተባሉ የህዝብ ኮንፈረንሶች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
"ኢትዮጵያውያን ዓለም የመሰከረላቸው እንደ ጥበብ ሻማ ሕብር ባጌጠ ባህላዊ ማንነት የተሳሰርን፣ በፍቅር አብረን የኖርን ሕዝቦች ነን" ብለዋል፤ የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ሂሩት ካሳ፡፡
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን 16 ብሄረሰቦች የሚገኙ ሲሆን ያልተዳሰሱ በርካታ ቱባ ባህሎች ባለቤቶች ናቸው፡፡ የግጭት አፈታት ባህላዊ ሥነ ስርዓት አላቸው፡፡ በአንድ መሠረታዊ ጉዳይ የተቀያየሙ እንደሆነ በባህላዊ መንገድ እረቀ ሰላም ያወርዳሉ፡፡
1440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሀዋሳ ከተማም በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ 1439ኛውን በዓል በከተማው በነበረው የፀጥታ ችግር ተሰብስበው ሶላት ማድረግ አለመቻላቸውን የጠቀሱ የዕምነቱ ተከታዮች የዘንድሮው ኢድ አልፈጥር የተለየ ነው ሲሉ ምክንያቶችን በመጥቀስ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡ ሀይማኖታዊ ነፃነትና መብታችን ከየትኛውም ጊዜ በላይ የተከበረበት ዓመት ነውም ብለዋል፡፡
"የአቃፊነትና የነፃነት ተምሳሌት ነው" የተባለው የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጨምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ጉዱማሌ ሶሬሳ ሶንጎ ተከብሯል፡፡
25ሺህ ለሚደርሱ ከጉጂ ዞኖችና ከአማሮ ቀበሌያት ለተፈናቀሉ ዜጎች፣ የተለያዩ አካላት የግል ጥረት በማድረግ ዕርዳታ እያደረጉላቸው መሆኑን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ተጎጂዎች ተናገሩ፡፡
ወደቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ገበያ በመገበያየት የቀድሞ የህዝብ ለህዝብና ማህበራዊ ግንኙነት መጀመራቸውን በጌዴዖ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የጭርቁ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በቀበሌው ቤቶቻቸው ከተቃጠለባቸው ዘጠኝ መቶ አባወራዎች ውስጥ የአምስት መቶ አባወራዎችን ቤት ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እንደሰራላቸው የሚገልፁ ዜጎች ወንጀለኞች ባለመያዛቸው ኑሯቸውን በሥጋት እንደሚመሩ አስረድተዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ