በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመሬት መንሸራተት 23 ሰዎች ሞቱ


በመሬት መንሸራተት 23 ሰዎች ሞቱ
በመሬት መንሸራተት 23 ሰዎች ሞቱ

በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ጥቅምት 2/2012 ዓ.ም ከለሊቱ ዐስር ሰዓት አከባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የልዩ ወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

የልዩ ወረዳው አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና የመንገሥት ኮሚውኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታከለ ተሰፉ፤ በአደጋው 23 የሚደርሱ የአምስት ቤተሰብ አባላት ሕይወት እዳለፈ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። አቶ ታከለ አያይዘው “ከሟቾቹ ውስጥ ዐስራ ሦስቱ ሴቶች ቀሪዎቹ ደግሞ ወንዶች ናቸው” ብለዋል።

በልዩ ወረዳው አመያ በተባለው ስፍራ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች የደረሰው ይህ አደጋ ነዋሪዎች በእንቅልፍ ላይ እያሉ በሌሊት በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ምክኒያት በመከሰቱ ምክኒያት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ኃላፊው ተናግረዋል።

የዐሥራ ሦስት ሰዎች አስክሬን በሰው ጉልበት ቁፋሮ መውጣቱንና የቀሪዎቹን ለማውጣት ኅብረተሰቡ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አቶ በላይ በቀለ የተባሉ በቦታው የሚገኙ ነዋሪ ገልጸዋል፡፡

የቀሪዎቸን አስክሬን የመፈለግ ሥራ የቀጠለ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ እንሰሳትም የአደጋው ሰለባ ሆነዋል።(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በመሬት መንሸራተት 23 ሰዎች ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:12 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG