በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ጣና ላይ ያለው ችግር የሁላችንም የኢትዮጵያውያን ችግር ነው" - ታከለ ኡማ

ም/ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ
ም/ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የአሥር ሚሊዮን ብር ልገሳ በከተማው አስተዳደር ስም አበረከቱ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የአሥር ሚሊዮን ብር ልገሳ በከተማው አስተዳደር ስም አበረከቱ፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች በባህርዳር
የአዲስ አበባ ወጣቶች በባህርዳር

ከንቲባው ከባህር ዳር እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች አመራሮች ጋር ትናንት የተወያዩ ሲሆን በንግግራቸውም ጣና ላይ ያለው ችግር የሁላችንም የኢትዮጵያውያን ችግር ነው፣ በጣና ሀይቅ ላይ የተጋረጠውን አስከፊ የእምቦጭ አደጋ ለመታደግ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው አያይዘውም አንድነታችንን የሚጠላው ጠላታችን ብቻ ነው፣ አንድነታችንን የሚጠሉ ኃይሎች ማኅበራዊ መገናኛ ላይ መሽገልዋል ሲሉም ተችተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

"ጣና ላይ ያለው ችግር የሁላችንም የኢትዮጵያውያን ችግር ነው" - ታከለ ኡማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG