በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት


ባህር ዳር
ባህር ዳር

“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለሰባዊ መብት ጥሰት ተዳርገን ቆይተናል” ሲሉ ከአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ አዲስ ራይ ማሰልጠኛ ተቋም ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ የመጡ ወጣቶች ገለፁ።

"ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለሰባዊ መብት ጥሰት ተዳርገን ቆይተናል" ሲሉ ከአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ አዲስ ራዕይ ማሰልጠኛ ተቋም ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ የመጡ ወጣቶች ገለፁ።

“ከመጣን ከወር በላይ ሆኖናል” የሚሉት ተፈናቃዎጭ “የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሚያስፈልገንን በሙሉ እዲሟላልን ትዛዝ ቢያስተላልፉም የበታች አስፈፃሚ አካላት ግን እያጉላሉን ነው” ብለዋል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት በበኩሉ፤“ተፈናቃዎቹን በዘላቂነት ለማቋቋም የብድርና የመስሪያ ቦታ ለመስጠት እያመቻቸው ነው" ይላል።

"ለጉልበት ብዝበዛና ሰብአዊ መብት ጥሰት ወጣቶች ዳረገን" ያሉትን የመከላከያና ብረታ ብረት ኢንጅነሪግ ኮርፕሬሽን ኃላፊዎችን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

“ሰርዶ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” የተባለ ድርጅት የሰው ኃይልና አቅም ግንባታ ኃላፊ ለጀርመን ድምፅ ዘጋቢ በሰጡ ቃል፤ "ወጣቶቹ በእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር ሥር ሆነው ወደተቀናጀ ግብርና ልማት እዲገቡ ጥረት ቢደረግም ልማቱ በመዘግየቱ ሊበተኑ ችለዋል" ይላሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:20 0:00
ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:14 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG