በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎንደር ዩንቨርስቲ ለ60 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠ

ወጣት ገብረ ኪዳን ሽባባው
ወጣት ገብረ ኪዳን ሽባባው

ጎንደር ዩንቨርስቲ በችግር ምክንያት የከፍተኛ ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ ለ60 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እየሰጠ መሆኑን የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፀ። ከ60ዎቹ ውስጥ 40ዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡

ጎንደር ዩንቨርስቲ በችግር ምክንያት የከፍተኛ ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ ለ60 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እየሰጠ መሆኑን የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፀ። ከ60ዎቹ ውስጥ 40ዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡

በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ነው እየተማሩ ያሉት። በዘንድሮው ዓመት ኢትዮጵያውያንን ብቻ የተቀበለ ሲሆን በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ለ450 በምሥራቅ አፍሪካ ለሚገኙ ችግረኛ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል ይላሉ ፕሬዚዳንቱ።

የሁለተኛ ዓመት የህግ ተማሪ የሆነው ወጣት ገብረ ኪዳን ሽባባው “ትምህርቴን ሳጠናቅቅ፣ ለአካል ጉዳተኞች የተነፈጉ መብቶች ላይ እሰራለሁ” ይላል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የጎንደር ዩንቨርስቲ ለ60 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG