በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባህር ዳር ነዋሪዎች ቅሬታ

ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል - ባህር ዳር
ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል - ባህር ዳር

"ከሆስፒታሉ ካርድ ከማውጣት ውጭ ምንም ዓይነት አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም። ምርመራ ከግል ሆስፒታል አድርጉ፣ መድሃኒት ከውጭ ግዙ ነው የምንባለው" ሲሉ በባህር ዳር ከተማ የፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተገልጋዮች ገለፁ።

"ከሆስፒታሉ ካርድ ከማውጣት ውጭ ምንም ዓይነት አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም። ምርመራ ከግል ሆስፒታል አድርጉ፣ መድሃኒት ከውጭ ግዙ ነው የምንባለው" ሲሉ በባህር ዳር ከተማ የፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተገልጋዮች ገለፁ።

ሆስፒታሉ ደግሞ ወደ 70 ሚልዮን ብር ግምት ያለው መድሃኒት ለነፃ ታካሚዎች ስለምሰጥ የመድሃኒት እጥረት አጋጥሞኛል፣ የመመርመሪያ መሳሪያዎችም አንሰውኛል፣ ያሉትም አርጅተዋል ይላል።

የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በበኩሉ ሆስፒታሉ የ44 ሚልየን ብር ዕዳ አለበት፤ ዕዳውን ካልመለሰ በዱቤ መድሃኒት አልሰጥም እያለ ነው።

የችግሩ ምንጭ የሆነው ጤና ቢሮው ለነፃ ታካሚዎች የሚሰጠውን ድጎማ ስላልሰጠኝ ነው ሲል የሆስፒታሉ ጤና ቢሮ ደግሞ ሆስፒታሉ እዚህ ኪሳራ ውስጥ የገባው በአመራሩ ዝርክርክ አሰራር ነው ይላል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የባህር ዳር ነዋሪዎች ቅሬታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:02 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG