በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ኤርትራ በብርቱ የመብቶች ጥሰት ተከሰሱ


የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊ የእ.አ.አ. 2015-2016 የዓለም ዙሪያ ይፋ እያደረጉ - ከትዊተር የተገኘ ፎቶ
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊ የእ.አ.አ. 2015-2016 የዓለም ዙሪያ ይፋ እያደረጉ - ከትዊተር የተገኘ ፎቶ

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የዓለምን ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ የፈተሸ ዘገባ የአሮፓዊያኑ 2015 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ማሽቆልቆሉን ገልጿል። በተለይ በአፍሪካ ቀንድ - በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሰብአዊ መብቶች በብርቱ የተጣሱበት ዓመት እንደነበረ ድርጅቱ ጠቅሷል።

የዓለምአቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ዘገባ እ.አ.አ 2015 ዓ.ም. በሰብዓዊ መብት ጥበቃ በዓለም ዙሪያ እንዳሽቆለቆለ ገልጿል። ወደ 400 ገጽ የሚሆነው መረጃ በአፍሪካ ውስጥ የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደታየ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠቅሷል።

በተለይም በአፍሪካ ቀንድ - በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሰብአዊ መብቶች በብርቱ የተጣሱበት ዓመት እንደነበረ ድርጅቱ ጠቅሷል። ሚሸል ካጋሪ በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድና የግሬት ሌክስ አገሮች ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር ናቸው። ኤርትራ በዓለም ስደተኞችን ከሀገር በማፍለቅ ከሶሪያና አፍጋኒስታን ቀጥሎ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

በመቀጠልም፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ብሔራዊ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ ማሸነፉን ከገለጹ በኋላ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻቸውን በሚያካሄዱበት ጊዜ መታሰር እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል። በኢትዮጵያ በነጻነት ሃስብን የመግለጽና የመድራጀት መብቶች እንዲሁም አጠቃላይ የዜጎች ይዞታን አስመልክተው ካጋሪ መግለጫ ሰጥተዋል።

በኦሮምያ ክልል እየተካሄዱ ያሉትን ተቃውሞዎችንም በማንሳት፣ ሚሸል ካጋሪ የኢትዮጵያ ጸጥታ ኅይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየወሰዱ ያሉትን እርምጃ፣ “ሰብአዊ መብትን የጣሱ” ድርጊቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሚሸል ካጋሪ በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድና የግሬት ሌክስ አገሮች ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር
ሚሸል ካጋሪ በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድና የግሬት ሌክስ አገሮች ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር

የአፍሪካ ሕብረት የአውሮፓውያኑን 2016 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብት ዓመት ብሎ ሰይሞታል። 2016 ደግሞ፣ በአፍሪቃ የተለያዩ ሰብአዊ መብትን ድንጋጌዎች የተላለፉበት እዮቤልዩ የሚከበርበት ዓመት ነው። ማለትም፣ የአፍሪካ ቻርተር በሰብአዊና በሕዝቦች መብት ላይ የተጻፈበትን 35ኛ ዓመት፣ ቻርተሩ የሚተገበርበት 30ኛው ዓመት እናም፣ የአፍሪካ ፍርድ ቤት የምስረታ 10ኛ አመቱን የሚያከብርበት ዘመን ነው። ሚሼል ካጋሪ፤ እነዚህ ሁሉ የመብት ድንጋጌዎች በዓሎች በሚከበሩበት አመት የአፍሪካ መሪዎች በቃላቸው እንዲገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቅርቧል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እ.አ.አ. 2015 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብት ጥበቃ በዓለም ዙሪያ እንዳሽቆለቆለ ይገልጻል
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እ.አ.አ. 2015 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብት ጥበቃ በዓለም ዙሪያ እንዳሽቆለቆለ ይገልጻል

ሳሌም ሰለሞን በቴሌፎን ሚሸል ካጋሪን አነጋግራ ያጠናቀረችው ዘገባ አለ፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ኢትዮጵያና ኤርትራ በብርቱ የመብቶች ጥሰት ተከሰሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG