በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ የጭካኔ ግድያ እንዲቆም ሂውማን ራይትስ ዋች ጠየቀ


ለዝሊ ለኮፍ -የሂውማን ራይትስ ዋች አፍሪካ ፕሮግራም ምክትል ዳይረክተር (ከፍሊከር የተገኘ ፎቶ)
ለዝሊ ለኮፍ -የሂውማን ራይትስ ዋች አፍሪካ ፕሮግራም ምክትል ዳይረክተር (ከፍሊከር የተገኘ ፎቶ)

ከሕዳር ወር 2008 ዓም ጀምሮ በሰፋት በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደዉን ተቃዉሞ የኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች በጉልበት እያፈኑት ነዉ ይላል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watach) ዛሬ ባወጣዉ ዘገባ።

ተቃዉሞዉ ከጀመረበት ሰሞን አንስቶ በየእለቱ ሰዎች እንደሚገደሉና በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ፥ በቁጥጥር ስር ሳሉ ስቃይ እንደሚፈጸምባቸዉም የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው ዘገባ አስታዉቋል። ዘገባውን በአማርኛ ለማምበብ ይህንን ፋይል ይጫኑ

ባለፈዉ ሳምንት ፍጻሜ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ቃለ ምልልስ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽንስ ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ፥ የመከላከያ ሰራዊት ከኦሮሚያ እንደማይወጣ ይሁንና ከተቃዋሚዎች እና ከመንግስትም በኩል ያለ አግባብ ሃይል በመጠቀም ሕግ የጣሱ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ሙሉዉን ዘገባ ያድምጡ።

በኦሮሚያ የጭካኔ ግድያ እንዲቆም ሂውማን ራይትስ ዋች ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG