በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በኢስታንቡል ጉባዔ ቀርበዋል


የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ጉባዔ በዛሬው ዕለት በቱርክ ኢስታንቡል ተከፍቷል። ​​የረድኤት ተቋማት መሪዎችና መንግሥታት በተወከሉበት በኢስታንቡሉ ጉባዔ የተገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በተመለከተ ለመድረኩ አቅርበዋል።

ለሁለት ቀናት የሚዘልቀው የዚህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጠራው ጉባዔ አቢይ ዓላማዎች አንዱ በመንግስታቱ ድርጅት ተቋም ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ አሰጣጥ መዋቅሮችን ለመፈተሽና ለማሻሻል ነው።

የረድኤት ተቋማት መሪዎችና መንግሥታት በተወከሉበት በኢስታንቡሉ ጉባዔ የተገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በተመለከተ ለመድረኩ አቅርበዋል

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበርያ የኢትዮጵያው ጽ/ቤት ወይም ኦቻ የእቅድና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ኃላፊ ቾይስ ኦኮሮ ማምሻውን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስለ ጉባኤው አስረድተዋል። ሳሌም ሰለሞን ኢትዮጵያን ለመታው ድርቅ በአሁኑ ወቅት እየተሰጠ ስላለው ምላሽና ጥረቶች አነጋግራቸዋለች። ዝርዝሩን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በኢስታንቡል ጉባዔ ቀርበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG