የፀረ ወባ ጥምረት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሀገሮች ሽልማት ሰጠ። ኤርትራ ከተሸለሚ ሀገሮች አንዷ ነች።
ዓመታዊው የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ባለፈው ዓመት ብቻ በ72 ሃገሮች የአጠቃላይ ነፃነት ሁኔታ ቀንሷል። የነፃነት ማሽቆልቆል ከተጀመረባቸው ዓመታትም የከፋው አምና እንደሆነም ዘገባው አክሏል።
የኤርትራው ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥታቸው በልዩ ልዩ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ዙሪያ በሚከተላቸው ፖሊሲዎች ላይ ማብራሪያና ገለጻ አደረጉ።
የኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች ኦሮምያ ውስጥ ተገድለዋል ያሏቸውን 140 ሰዎች ጉዳይ በቅርበት እንዲፈትሹ ሲቪከስ ተብሎ የሚጠራው የዜጎች ተሣትፎ ዓለምአቀፍ ጥምረት ጥሪ አሰምቷል፡፡
የሰብአዊ መብት ድርጅቱ በመግለጫው የጠቀሰው አኃዝ፣ እስካሁን መንግሥት ካረጋገጠው ቁጥር ሆነም ሌሎች የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ከዚህ በፊት ከጠቀሱት ቁጥር በእጅጉ የላቀ ነው። መንግሥት ግን በዚህ ሰልፍ ምክንያት የ5 ሰዎችን ሞት ብቻ ነው እስካሁን ድረስ ያመነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸዉን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ ዓለም አቀፉ የመብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስከ ፊታችን የካቲት 9, 2008 ዓለም አቀፍ ማህበረስብ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደብዳቤ እንዲጽፍ ጥሪ አቀረበ። ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን መፍታት አለበት ሲል ጥሪ አድርጓል። የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ተማሪዎች ጋዜጠኞችና ሌሎች በኢትዮጵያ እስር ቤት ዉስጥ ስቃይ እየተፈጸመባቸዉ ነዉ የሚል ስጋቱን አሰምቷል ድርጅቱ።
የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል።
ሁለት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ከ30,000 ዶላር በላይ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ ሰብስበው በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል። ጎ-ፈንድ-ሚ ወይም (GoFundMe) በግርዱ ወደ አማርኛ ሲመለስ፤ “ድጋፍህን ስጠኝ፤” በሚል ስያሜ በሚታወቀውና በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከ1 ቢልዮን ዶላር በላይ በ 365 ቀናት ውስጥ ሊሰበስቡ የሚችሉበት ድረ-ገጽ ነው።
ሁለት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ከ30,000 ዶላር በላይ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ ሰብስበው በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል።
ሁለት በዳያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለተራቡ ወገኖች ሰብስበው ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረከቡ።
የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን ድርጅት(CPJ) ትናንትና ማታ በዓለም አቀፍ ዙሪያ መረጃ የብዙኅን ነፃነት እንዲከበር ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ሽልማት በኒው ዮርክ አበረከተ።
የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ ዳይረክተር ሶንያ ሩትዘል (Sonja Ruetzel) የመድረኩን ዓላማና እአአ በየካቲት ሁለትና ሦስት በአዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማእከል የስብስባ ፕሮግራሙን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።
የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ (Aid International Development Forum/AIDF)ዳይረክተር ሶንያ ሩትዘል (Sonja Ruetzel) የመድረኩን ዓላማና እአአ በየካቲት ሁለትና ሦስት በአዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማእከል የስብስባ ፕሮግራሙን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) የአስቸኳይ መልስ ፋንድ ክፍል ሰርፍ(CERF) ለኢትዮጵያ ከገጠሙት ሁሉ የከፋ በሆነ ድርቅ ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ ትናንትና ሰጠ።
ጆንሰን ማልዳን የታፈሰ አበበን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተሉ ያሉ መርማሪ መኰንን ናቸው። "እኔ በአሁኑ ተጠርጣሪዎቹን እያፈላለግሁ ነው የምገኘው። ሌላ መረጃ የለኝም" ብለዋል።
በዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያ ለመሳተፍ ወደ ቦትስዋና በቅርብ ለሄዱት 10 የኤርትራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት የቦትስዋና መንግስት ፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል። ስፖርተኞቹ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ቡድን ጋር ከተጫወቱ በውኃላ ነው ወደ ሃገራቸው በሚወስዳቸው አውሮፕላን ላይ አንሳፈርም በማለት በቦትስዋና ጥገነት የጠየቁት።
ሰማንያ ሶስት ከመቶ ምርጫ በማሽነፍ ለሁለተኛ ግዜ ተመርጠው ስልጣናቸውን እንዲቀጥሉ የተመረጡት ፕረዚደንት አላሳን ዋታራ በወደፊት የስልጣናቸው ግዜ የሃገሪቱ ረሃብን በግማሽ ለመክፈልና ብሔራዊ መሰናኘትን ወይም መግባባትን ለማስፈን እንደሚጥሩ ገልጸዋል።
በአነጎላ የረሃብ አድማ ሲያደርግ የሰነበተው ታዋቂ የራፕ ድምፃዊና (rapper) የፖለቲካ ታጋይ፣ ልዋቲ ቢራዎ (Luaty Beirao) ከ36 ቀናት በኃላ አድማውን አቋርጧል። የራብ አድማውን ለማቆም ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ለጤናው ሰግተው ያቀረቡት ተማፅኖ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በዚህ ሳምንትየጀኔቫ ሚኒስተሮች፣ የክልል አስተዳዳሪዎች እና ከፍተኛ ሃላፊዎች በአውሮፓ በብዛት የሚያልፉት ስደተኞችና ፍልሰተኞች እንዴት ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ እንደሚሸጋገሩ ለመወያየት እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ሪኪ ሽርዮክ (Ricci Shryock) በሚላን የከተማዋ ዋና የስደተኞችና ፍልሰተኞች መሸጋገርያ ጣብያ የሚሰራ አንድ ኤርትራዊ ወጣት አነጋግራ የላከችው ዝርዝር።
ተጨማሪ ይጫኑ