በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴይትስ ኤምባሲ ያሰራው የባህልና የፈጠራ ማዕከል በዛሬው እለት ተመርቆ ከፈተ። ማዕከሉ በጆን ሲ ሮቢንሰን (Col. John C. Robinson) ስም ነው የሚጠራው። ኮረኔል ሮቢንሰን በጣልያን ወረራ ጊዜ የኢትዮጵያ ጦር አየሮችን የሚያበር የነበረ ታዋቂ አውሮፕላን አብራሪ ነበር።
የዩናይትድ ስቴይትስ ኤምባሲ በአዲስ አበባ የባህልና የፈጠራ ማዕከል ከፈተ
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ የማዕከሉን መከፈት ምክንያት በማድረግ በፌስቡክ የቪድዮ መልእክት አሳልፈዋል። "የአሜሪካ አምባሳደር እንደመሆኔ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮረኔል ጆን ሲ ሮቢንሰን ስም የተሰየመውን ማዕከል መከፈት ሳበስር በጣም ደስታ ይሰማኛል። በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር ተባብረን በመስራታችንም ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል።" ብለዋል።
"ወደ ማዕከሉ መጥታችሁ እንድትጎበኙ እጋብዛችኃለው። ይህ ማእከል እንደ ዕውቀት መቅሰሚያ እንዲሆን፣ እንድትፈጥሩ፣ እንድታቅዱበት እናም አዳዲስ ሃሳቦችን በአለማችን ላሉ ወቅታዊ ችግሮች መፍትሄ ይገኝበት ዘንድ የመወያያ መድረክ ይሆናል ተብሎ የተሰራ ማዕከል ነው።" ብለዋል አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ።
እስክንድር ፍሬው ዝግጅቱን ዛሬ ማምሻውን ተከታትሎ ከሔኖክ ሰማእግዜር ቃለ-ምልልስ አድርጎ ነበር። ቃለ-ምልልሱን እና አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ ያስተላለፉትን መልእክት ያጠቃለለ ዘገባ አለ፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።