በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ሐገር መመለስ፡- ከውቅያኖስ ውሽንፍር የተረፉ ስደተኞች የወደፊት እጣ


ወደ ሐገር መመለስ፡- ከውቅያኖስ ውሽንፍር የተረፉ ስደተኞች የወደፊት እጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:19 0:00

ወደ ሐገር መመለስ፡- ከውቅያኖስ ውሽንፍር የተረፉ ስደተኞች የወደፊት እጣ

በሜዲትራንያን ባህር ከደረሰ የጀልባ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያዊና ሶማሊያዊ ወጣቶች ትናንት ግሪክ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በባህር ላይ ሰዎች ሰምጠው ሲሞቱ እንዳዩ ተናግረዋል።

በሜዲትራንያን ባህር ከደረሰ የጀልባ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያዊና ሶማሊያዊወጣቶች ትናንት ግሪክ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በባህር ላይ ሰዎችሰምጠው ሲሞቱ እንዳዩ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) እሮብ እለትበህይወት ከተረፉት ሰዎች ባገኘው መረጃ መሰረት የሞቱት ሰዎች 500ሊደርሱ እንደሚችሉ ያደረበትን ስጋት ገልጿል።

የ25 ዓመቱ ወጣት ሙዓዝ ማህሙድ ስለ ሁኔታው እንዲህ ይላል፣ "ትልቁ ጀልባ መስመጥ ሲጀምር እኔ ጀልባው ውስጥ ነበርኩ። የሁለት ወር ልጄና የ20 ዓመት ሚስቴም ከኔ ጋር ነበር የሚጓዙት። በምንጓዝበት ወቅትመርከቧ መስመጥ ጀመረች። ተጭነው የነበሩት ሰዎች ውቅያኖሱ መሃልሰምጠው ሁሉም ሞቱ፣ ከለሊቱ ሰባት ሰአት ነበር።"

"አንዳንድ ሰዎች ለመዋኘት ሲሞክሩ ማየት እንችል ነበር። ሁለት ጀልቦችስለነበሩ፣ ወደ ሁለተኛዋ ጀልባ ለመዋኘት ሲሞክሩ ነበር። እኛምህይወታችንን ለማዳን ወደ ሁለተኛዋ ጀልባ ዋኘን ። ሶማሌዎች ነበሩ ጀልባዋላይ እና ወደ እኛ የሆነ ነገር ጣሉልን። አስር ሰዎች ነበርን የምንዋኘው፤ ከውኃው አውጥተው ህይወታችንን አዳኑን። ከዛም እኔም የሁለት ሰዎችንህይወት ለማዳን ቻልኩ።" ብሏል።

የሶማልያው ወጣት መውሊድ ኢስማም በጉዞው የተመለከተውን ሲገልጽ፣ "ሰዎች ሲሞቱ በአይናችን አይተናል። እኔም ከቤተሰቤ ጋር የተሰበረችውጀልባ ውስጥ ነው የነበርኩት። አምላክ ነው ያወጣኝ! ሌሎች ሰዎችስለረዱኝ። እንኳንም 41 ሰዎች ተረፍን። እኔ የፈለግኩት ቤተሰቤን ወደሁለተኛዋ ጀልባ ለማሸጋገር ነበር የነበረኝ ሃሳብ፣ ነገር ግን አልተሳካልኝም።"

"ጉዞውን ለመጨረስ ፈልገን ነበር ግን አልቻልንም። ያልቻልንበትም ምክኒያትየተቀሩት ቤተሰቦች ሁሉም ስለሞቱ ነው። አንዳዶቹ ሰዎች አሳርፈንእንድንቀጥል አበረታተውን ነበር፣ ነገር ግን በፍጹም ለመቀጠልአልቻልንም።" ብሏል።

UNHCR ባወጣው መግለጫ ከአደጋው የተረፉት 41 ሰዎች መካከል 23 ከሶማልያ፣ 11 ከኢትዮጵያ፣ 6 ከግብጽ እና አንድ ከሱዳን መሆናቸውን ገልጿል።

XS
SM
MD
LG