በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ የጅቡቲ የጦር እሥረኞችን ለቀቀች


 የራስ ዱሜራ ደሴቶችና የባህር ግዛት የሚያሳን የኤርትራና የጅቡቲ ካርታ
የራስ ዱሜራ ደሴቶችና የባህር ግዛት የሚያሳን የኤርትራና የጅቡቲ ካርታ

ኤርትራ ላለፉት ስምንት ዓመታት ይዛቸው የቆየቻቸውን አራት ጂቡቲያዊያን የጦር እሥረኞችን ለቅቃለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የጦር እሥረኞቹን መፈታት ዜና በአድናቆት መቀበላቸውን አስታውቀዋል። የቀሪዎቹ እሥረኞች ደኅንነት እንደሚያሰጋት ግን አሜሪካ ገልፃለች።

ኤርትራ ላለፉት ስምንት ዓመታት ይዛቸው የቆየቻቸውን አራት ጂቡቲያዊያን የጦር እሥረኞችን ለቅቃለች።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የጦር እሥረኞቹን መፈታት ዜና በአድናቆት መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

የቀሪዎቹ እሥረኞች ደኅንነት እንደሚያሰጋት ግን አሜሪካ ገልፃለች።

በኤርትራና በጂቡቲ መካከል የዛሬ ስምንት ዓመት (በሰኔ 2000 ዓ.ም.) ተካሂዶ በነበረው የድንበር ግጭት 19 ወታደሮችን ይዛ እንደነበርና የተወሰኑት ከተያዙ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንዳመለጡ በዩናይትድ ስቴትስ የጂቡቲ አምባሣደርና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሃገሪቱ ቋሚ ተጠሪ የሆኑት ሞሐመድ ሰዒድ ዱአሌ ገልፀዋል።

ራስ ዱሜራ፤ የኤርትራና የጂቡቲ ካርታ
ራስ ዱሜራ፤ የኤርትራና የጂቡቲ ካርታ

የጦር እሥረኞቹ እንዲለቀቁ ያደራደረችው ቃታር ስትሆን የተፈቱት ወታደሮች ባለፈው ሣምንት ዓርብ፣ መጋቢት 2/2008 ዓ.ም በቃታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼኽ ሞሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል ጣኒ አጃቢነት በቃታር አየር መንገድ አይሮፕላን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ታውቋል

እሥረኞቹ በያዙባቸው ዓመታት ከመንግሥታቸው ባለሥልጣናትና ከቤተሰቦቻቸውእንዳይገናኙ ተነጥለው ብቻቸውን ተይዘው መቆየታቸውን የጂቡቲው አምባሳደር ዱአሌ አስታውቀዋል።

የቃታር መንግሥት ላደረገው ጥረት አሥመራ አድናቆቷን ገልፃለች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ኤርትራ የቃታርን አደራዳሪነት እንደምትቀበል ከመነሻው ጀምሮ ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡ የቃታር ሽምግልና ሰባት አንቀፆችን የያዘ ሲሆን አንቀፅ ሦስት የጠፉ ሰዎችንና የጦር እሥረኞችን የሚመለከት ነው፤ ብቸኛው ሂደትም የቃታር ሽምግልና መሆኑን ያለመዛነፍ ስንናገር ቆይተናል” ብለዋል።

ጂቡቲ 19 ኤርትራዊያን የጦር እሥረኞችንና የጦር ግንባር ከድተው እጅ የሰጡ ወታደሮችን መያዟን አምባሳደር ዱአሌ ገልፀው በአውሮፓ አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሺነር - ዩኤንኤችሲአር እንዳስረከበቻቸው አመልክተዋል። ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴና ሌሎችም ዓለምአቀፍ ድርጅቶች የጦር እሥረኞቹን በየወቅቱ ይጎበኟቸው እንደነበረ የጂቡቲው አምባሣደር በአፅንዖት ተናግረዋል። ደኅንነታቸውና ሰብዕናቸው በሚገባ ተጠብቆ እንተያዙም አስረድተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የጦር እሥረኞቹን መፈታት ዜና በአድናቆት መቀበላቸውን አስታውቀዋል። የቀሪዎቹ እሥረኞች ደኅንነት እንደሚያሰጋት ግን አሜሪካ ገልፃለች።

የእሥረኞቹ መፈታት በሁለቱ ጎረቤት ሃገሮች መካከል የግንኙነትን መሻሻል ለማስገኘት የተወሰደ አንድ እርምጃ ነው ብለው እንደሚያምኑ የጂቡቲው አምባሣደር ዱአሌ አስታውቀዋል።

“በሁለቱ ሃገሮች መካከል የትብብር ንግኙነቶች መኖር ብቸኛው የሚታይ አማራጭ ነው” ሲሉም የኤርትራው የመንግሥታቱ ድርጅት አምባሣደር ግርማ አስመሮም ተናግረዋል።

የኤርትራና የጅቡቲ ካርታ
የኤርትራና የጅቡቲ ካርታ

በራስ ዱሜራ ደሴቶችና በባህር ግዛት መካለል ጉዳይ ላይ በኤርትራና በጂቡቲ መካከል በተነሣው የይገባኛል ጥያቄና ውጥረት ምክንያት የሁለቱ ሃገሮች ወታደሮች የዛሬ ስምንት ዓመት ውጊያ ውስጥ ገብተው እንደነበረ ይታወሣል።

ለተጨማሪ መረጃዎች፣ የሂውማን ራይትስ ዋች ዘገባን ይህንን ፋይል በመጫን ያንብቡ፣ ገልፍ ታምይስ የተባለ ድረ-ገጽ የዘገበውን ዜና ለማምበብ ይህንን ፋይል ይጫኑ

XS
SM
MD
LG