በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥትና የአለም ዓቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለድርቁ እርዳታ ወደ $1.4 ቢልዮን ለማሰባሰብ ጥረት እያደረጉ ነው


ወደ 1.7 ሚልዮን የሚሆኑ ነፍሰ ጡርና እና የሚያጠቡ እናቶች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል
ወደ 1.7 ሚልዮን የሚሆኑ ነፍሰ ጡርና እና የሚያጠቡ እናቶች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል

በድርቁ ምክኒያት ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለተረጂነት ተጋልጠዋል። የተባበሩት መንሥታት ድርጅት የ 90 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የአለም ዓቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ድርቅ እርዳታ ወደ $1.4 ቢልዮን ለማሰባሰብ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

የድርቅ ሁኔታ በኢትዮጵያ ዶዶታ ወረዳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:06 0:00

መንግሥትና የእርዳታ ድርጅቶችም ድርቁ በኤል ኒኞ ምክኒያት እንደተባባሰ ገልጸዋል። በድርቁ ምክኒያት ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለተረጂነት ተጋልጠዋል። የተባበሩት መንሥታት ድርጅት የ 90 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።

በዶዶታ ወረዳ አርሲ ዞን ነዋሪ የሆኑት ገበሬ አቶ አህመድ ሁሴን በአከባቢው ያጋጠመውን ሁኔታ ሲገልጹ "የእርሻ ሁኔታው አሁን ይሄ ማሳ እንደሚታየው፣ ያው እንዳረስን በድርቅ ምንክኒያት ምንም ውጤት ሳላገኝ እንደው በነጻ ምንም ሳይበቅል ነው የቀረው። " ብለዋል።

ፖል ሃንድሊ በኢትዩጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች የኦቻ ክፍል ሃላፊ
ፖል ሃንድሊ በኢትዩጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች የኦቻ ክፍል ሃላፊ

ፖል ሃንድሊ በኢትዩጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች የኦቻ ክፍል ሃላፊ ናቸው። "ባለፉት አመታት በተለያዩ ቦታዎች ዝናብ አልዘነበም። በእርሻ ላይ እናም በሚጠጣ ውኃ እጥረት ላይ እንደምታ አለው። ሰዎች ውኃ የሚያገኙበት ጥልቅ ካልሆነ ጉድጓ ስለበር፣ በአሁኑ ጊዜ እሱም ደርቋል። በዚህም ምክኒያት ሰዎች ከመኖርያቸው እየተፈናቀሉ ነው።" ብለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ ገበሬ ገና ገለታ ከብት ያረባሉ። ድርቁ ስለደቀነው ችግር "ከብቶቼ ከመመንመናቸው የተነሳ ማንም ሰው ከኔ ሊገዛ አይፈልግም። ልሸጣቸውም አልቻልኩም። ገንዘብ ባገኝ ኖሮ ምግብ እገዛበት ነበር።" በማለት ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አምና ለሕዝቡ ምግብ ለማቅረብ $272 ሚልዮን ዶላር ለእርዳታ አውሏል። በዚህ አመት ደግሞ $109 ሚልዮን ዶላር የድርቅ ችግሩን ለማቃለል ጥረት እያደረገ መሆኑ ታውቋል።

በኢትዮጵያ የአነስተኛ ይዞታ ገበሬዎች እና እረኞች በዝናብ ላይ ነው የሚተማመኑት። እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ከ 400,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በዚህ ድርቅ ምክኒያት የተመጣጠነ የምግብ እጦት በዚህ አመት ብቻ እንደተጠቁ ተነግሯል። ወደ 1.7 ሚልዮን የሚሆኑ ነፍሰ ጡርና እና የሚያጠቡ እናቶች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም ተጠቅሷል። ሂደቱን ለማቀላጠፍ የዓለም የምግብ ፕሮግም (WFP) ከሶማሊላንድ ከበርበራ ከተማ ምግብ እያስግባ መሆኑም ታውቋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG