በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት የሚያመሳስላቸው የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ይዞታ


ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው /ፎቶ - ከonedayseyoum.com ድረ-ገጽ የተገኘ/
ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው /ፎቶ - ከonedayseyoum.com ድረ-ገጽ የተገኘ/

የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን በዛሬውለት ሲከበር፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ምንም እንኳን የጋዜጠኞች ይዞታቸው ቢለያይም “አፋኝ” መንግስታት መሆናቸው ነው የተስተጋባው። የአለም የመገናኛ ብሀን ነጻነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ የጋዜጠኞች ይዞታና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ሁኔታ የሚያሳስባቸው የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የተለያዩ ዘገባዎችን አውጥተዋል።

ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው። 14 ዓመትና 226 ቀናትና 15 ሰዓታት በላይእስካሁን ቤተሰብ ሳይጠይቀው በእስር ላይ ቆይቷል።

በህይወት መኖሩን የሚያውቅ ማንም ሰው የለም። በድረገጽ የእህቱ ልጅ የ19 ዓመቷ ቨኔሳ በርኸ የኤርትራን ቴሌቭዥን ከመሰረቱት አንዱ እንደሆነ የምትናገረው አጎቷ ስዩም ጸሃየን ስቃይና ሰቆቃ በማስታወስ፤ እሱና ሌሎች ኤርትራዊ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ ላይ ትገኛለች።

"የሰጡን ማብራሪያ የለም፣ ፍርድ ቤት አልሄደ፣ ከቤቱ ሲወስዱት እንኳ ለምን እንደሚታሰር አልተገለጸለትም። የት እንዳለ አያውቁም፤ በህይወት መኖሩን አያውቁም፤ በተለይ ደግሞ ቅርብ የቤተሰቡ አባላትም ምንም መረጃ የላቸውም። ልጆቹም ባለቤቱም አባታቸው የት እንደሚገኝ አያውቁም። በጣም አሳዛኙ ሁኔታም ይሄ ነው፤ አሰቃቂ ሁኔታ ነው።" ብላለች።

ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው //ፎቶ - ከonedayseyoum.com ድረ-ገጽ የተገኘ/
ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው //ፎቶ - ከonedayseyoum.com ድረ-ገጽ የተገኘ/

​ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

​ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከምርጫ 97 ጀምሮ ለዓመታት ሲታሰርና ሲፈታ፤ መልሶ ሲታሰርቆይቷል። በአሁኑወቅት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ በተባለበት የሽብር ወንጀልየተፈረደበትን የ18 ዓመታት እስራት 4ኛ አመት ይዟል።

እነዚሁ ሁለት ጋዜጠኞች በሀገራቸውም ሆነ በዓለም ዙሪያ ብቸኞች አይደሉም። በዓለም ዙሪያ ከሰባት ሰዎች መካከል ስድስቱ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ባልተጠበቀባቸውና የጋዜጠኞች ደህንነት ዋስትና በሌለባቸው ሀገሮች ይኖራሉ። በዓለም ዙሪያ ላለፉት 12 ዓመታት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ያለማቋረጥ ማሽቆልቆሉን ባለፈው ሳምንት በዋሽንተን ዲሲ በፍሪደም ሀውስ ይፍ የሆነ ጥናት ጠቁሟል።

በፓሪስ መሰረቱን ያደረገውድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን አርማ (RSF)
በፓሪስ መሰረቱን ያደረገውድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን አርማ (RSF)

በፓሪስ መሰረቱን ያደረገውድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን RSF የአፍሪካ አጥኝ ክሌያ ካን ስራይበር (Clea Kahn-Sriber) ሁኔታውን ሲያስረዱ፣ "ዋናው የችግሩ መንስኤ በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው ያለ አግባብ የሰውነት ቅጣት በአለማችን በብዛት ይታያል። በተለይም በላቲን አሜሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ሃገሮች ተስፋፍቶ ይታያል። ይህ ከህግ ውጭ የሆነ በጋዜጥኞች ላይ የሚደርሰው ቅጣት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቀና በጋዜጠኛ ህይወትም ሆነ ስራ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረይገኛል። አሁን እኛ በመስራት ላይ ያለነው በግል የሚዲያ ስራ ላይ ያለውን ጫና በተለይም በኢኮኖሚና በፖለቲካ ላይ ያለውን ቁጥጥር ላይ ነው።" ይላሉ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ማሽቆልቆል ከሚታይባቸው ሀገሮች መካከል ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። በዚህ ሳምንት ይፋ የሆኑ ዘገባዎችም የሚያስረዱት ይሄንኑ ነው። የፍሪደም ሃውሷ ጄኔፈር ደናም ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ቃል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ በዓለም የመገኛና ብዙሃን ነጻነት ሰንጠረዦች ስማቸው በበጎ የማይነሳባቸውን ምክንያት አስረድተዋል።

"ከዚህ ቀደም ጋዜጠኞች በነጻነት እንዲሰሩ የሚያስችል ድባብ ተፈጥሮ ነበር። በአሁኑ ወቅት ቁልፍ የተባሉ ጋዜጠኞችና አዘጋጆች ታስረዋል፣ አንዳንዶቹ እንዲያውም ለብዙ አመታት ታስረው ይገኛሉ። የነጻ የመገናኛ ብዙሃንን መብት የሚጠብቅና የሚያከብር ሕግ በወረቀት ቢኖርም፣ በተግባር ላይ ሲውል አይታይም።" ማለታቸው ይታወሳል።

ኤርትራ በአፍሪካም ሆነ በዓለም የከፋ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ይዞታ የሚታይባት ሀገር እንደሆነች ድንበርየለሽ የጋዜጠኞች ቡድን (RSF) ጥናት ይጠቁማል። ለመሆኑ ኤርትራ እንደ ሰሜን ኮርያ ካሉ እጅግአፋኝና ከውጭ ሀገራት ጋር ያሏቸው ግንኙነቶች የተቋረጡአስተዳድር ካለባቸው ሀገሮች እንዴት የከፋች ተብለው ተጠይቀውሲመልሱ። ኤርትራ ከሰሜን ኮሪያም በከፋ መልኩ መረጃ እንዳይወጣተቆልፎ የተያዘባት ሀገር በመሆኗ ነው ሲሉ አስረድተዋል። የኤርትራ መንግስት የመገናኛ ብዙሃን በውጭ እርዳታ እንዲቋቋሙስለማይፈልግ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚሰጠውን ምላሽ የRSFአጥኝ ክሌያ ካን ስራይበር “መመጻደቅ” ብለውታል። "የኤርትራ መንግስት እንደዚህ አይነት ገደብ ሲጠቀሙ አያምርባቸው ምክንያቱም ከአውሮፓ ህብረት ሚልዮኖች በየአመቱ ገንዘብ እየተቀበሉ መንግቱን በስልጣን ላይ ያቆያሉ። በሀገራዊ ወታደራዊ አገልግሎት ምክንያት፣ በወጣቱም መዋእለ ንዋይ ስለማያፈሱ ምንም ለውጥ ሊያመጡ አልቻሉም። ይህን እንደ ምክንያት ነው የሚጠቀሙበት ። ጋዜጠኞች በነጻለመስራት እንደማይችሉ ለማድረግ ሆነ ተብሎ የሚደረግ ነገር ነው። የኤርትራን ኢኮኖሚ ግምት ወስጥ ስናስገባ ማንም ሰው ራሱን ችሎ ሰርቶ ነጻ የመገናኛ ብዙሃንን መፍጠር የሚችልበት ሁኔታ የለም።" ብለዋል።

በኒውዮር መሰረቱን አድርጎ ለጋዜጠኞች መብት የሚታገለው ቡድን (CPJ) ባለፈው ሳምንት ባወጣው የመገናኛ ብዙሃን ስራዎች ላይቅድመ ምርመራ ከሚያከናውኑ ሀገሮች መዝገብ ላይ የመጀመሪያዋኤርትራ ስትሆን፣ ሰሜን ኮርያ እና ሳዑዲ አረብያ ሁለተኛና ሦስተኛተብለዋል። ኢትዮጵያ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተጠቅሳለች። ኮርትኒ ራዴክ የ(CPJ) የመብት ሞጋች ቡድን ኋላፊ ናቸው። የአፍሪካቀንድ ሀገሮች በቅድመ-ምርመራ ሰንጠረዥ ላይ ግንባር ቀደም የሆኑባቸውን ምክንያቶች ሲገልጹ፣ "ከአፍሪካ አገሮች ሁሉ በግንባር ቀደም ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ስማቸው ሊጠቀስ የበቃበት ምክኒያት ብዙ ጋዜጠኞችን በማሰራቸው ነው። የኢንተርኔት ገደብ በማስፈራቸውንና፣ ነፃ የመገናና ብዙሃን ባለመኖራቸውም ጭምር ነው። እንዲያውም የመገናኛ ብዙሃን የሉም ቢባል ይሻላል። ኤርትራ በጣም ዝቅተኛ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ስርጭት አላት ብለናል። በነዚህ ምክንያቶች ነው ቀዳሚዎቹ አገሮች የሆኑት።" ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት በሳምንቱ መጨረሻ ባወጣው መግለጫ። የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ-ሽብር ህጉንበመጠቀም ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በስፋት ማሰሩ እንዳሳሰበው አስታውቋል። የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ይላሉ የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን አጥኚ ክሌያ ካን ስራይበር፤ በጥቅል የመብትና የፖለቲካ አፈና መሳሪያ እንዲሆን ደካማ የፍትህ ተቋማትና ጠንካራ የፖለቲካ ፈቃድና ጣልቃ ገብነት ፈቅዷል ይላሉ።

"መቃወምሽ በታወቀበት ፍጥነት ወይም ስለአንድ መንግስትንስለሚቃወም ነገር በዘገብሽበት ፍጥነት በአሽባሪነት ወንጀል ተጠያቂያደርጉሻል። በመቀጠልም ከባድ የወንጀል ክሱ ይቀጥላል።በወንጀለኝነት በመክሰስ ብጫ አያበቃም፡ በተከሳሽ አካባቢ የነበሩትንሰላማዊ ሰዎች ሁሉ ይነካል።" ብለዋል።

"በመጀመሪያ ማንኛውም ለፍርድ የሚቀርብ አሸባሪ እንኳ ቢሆንፍርዱን ለማክበድና ከባድ ቅጣትን ለመጣል እንዲያመቻቸውከአሽባሪነት ጋር ያያይዙታል። እንዲሁም ፍርድ ቤት ተከሳሽከመቅረቡ በፊት ያለውን በእስር የመቆያ ጊዜ በማራዘም ስለጉዳዩእንዲናዘዝ ያድስገድዱታል።" ይላሉ።

መደበኛ የሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ስርጭቶችን ማለትም የቴሌቭዥንና ሬድዮ ሞገዶችን በማፈን የሚታወቁ እንደ ኢትዮጵያ ያሉመንግስታት፤ በድረ-ገጽም ጭምር የስለላ መርጃዎችን በመልቀቅና ገጾችን በመዝጋት በተደጋጋሚ ይወቀሳሉ። በኢትዮጵያና ኤርትራ ያለውን ሁኔታ ሔኖክ ሰማእግዜርና ሳሌም ሰለሞን በሚከተለው ዘገባ ይዳስሳሉ።

የኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት የሚያመሳስላቸው የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ይዞታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:06 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG