የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ሰራተኞች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲራዘም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጠይቀ። እስካሁን ወደ 80 ሺህ የሚሆኑ ለመመለስ የጎዞ ሰነድ የወሰዱ ሲሆን፤ ከ25ሺህ በላይ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የማህበረሰቡ መሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።
የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ሠራተኞች ወደየሀገራቸው እንዲመለሱ ያወጣው የ90 ቀናት ጊዜ ገደብ 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እስካሁን ወደ 80 ሺህ የሚሆኑ ለመመለስ የጎዞ ሰነድ ወስደዋል፤ ከ25 ሺህ በላይ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ይላሉ የማህበረሰቡ መሪዎች። የጉዞ ሰነድ ባለመውሰዳቸው በሪያድ አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች በሳውዲ ፖሊስ መታሰራቸውን የገለጹየኢትዮጵያ ኢምባሲ በፍጥነት እንዲደርስላቸው ጥሪያቸውን አሰምተዋል።
የ86 አመት አዛውንት አሰሪዋን ገድላለች በሚል ተጠርጥራ በሊባኖስ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የምትገኘው ትዕግስት ሻሌ ባሊጉ ፍርድ ቤት አለመቅረቧንና አሁንም በእስር ላይ መሆኗን የኢትዮጵያ ቆንስላ አምባሳደር ሃሊማ ሞሃመድ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገለጹ። የ26 ዓመት ተጠርጣሪዋ ትእግስት ሻሌ ባሊጉ የህግ ድጋፍ እንድታገኝ ቆስላ ጽ/ቤቱ እንደሚሰራ አምባሳደሯ ገልጸዋል። ከበታች ያለውን ተንቀሳቃሽ ምስል በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።
የ86 ዓመቱ ሳልማን ኽሂኣሚ ባለፈው እሁድ ሌሊት በደቡብ ሊባኖስ ጂባል ኣልቦቶም በተባለ ከተማ በመኖሪያ ቤታቸው ተገድለው መገኘታቸውን የሊባኖስ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።በቤት ሰራተኝነት ለ9 ወራት ከአዛውንቱ ጋር የኖረችው የ26 አመቷ ኢትዮጵያዊት በወንጀሉ ተጠርጣሪ ሆና በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።በቅርቡ ነፍሰጡር አሰሪዋን በመግደል ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ስለምትገኘው ወጣት ሰፋ ያለ ዘገባ ይኖረናል።ይህች ወጣት በደረሰን የተረጋገጠ መረጃ መሰረት በህይወት አለች።
በማላዊ ‘ዝማሬ ለሳንቲም’ በሚል በተዘጋጀው ዘመቻ ላይ የሃይማኖት ዘማሪው በሃገሪቱ ለሚገኘው የህፃናት የካንሰር ህክምና ይውል ዘንድ ከ10,000 ዶላር በላይ በጥቂት ቀናት ውስጥ ማሰባብሰብ ችሏል።
ሳሙኤል መርጋ የ18 አመት ወጣት ነው። በርካታ ተንቀሳቃሽ ሞዴል ሮቦቶችን ሰርቷል። ባለፈው አመት ህንድ ከሚገኘው በሮቦት ፈጠራና በህዋ ምርምር ተሰጦ ካላቸው አለም አቀፍ ወጣቶች የስልጠና፣ ትምህርትና የሰርቶ ማሳያ ውድድር እድሎችን ከሚሰጠው ከስፔስ ዲቨሎፕመንት ኔክሰስ/Space Development Nexus/ኩባንያ ባዘጋጀው ውድድር ከ20 ወጣቶች በአንደኝነት አሸንፏል። ከሁለት ወራት በፊትም በዛው በህንድ አለም አቀፍ ውድድር በድጋሚ የአንደኝነት ደረጃ ይዞ አሸንፏል።
በየአመቱ በየካቲት ወርየሚደረገው ‘ጉማ’ የፊልም ሽልማት በዘንድሮውም ባለፈው ሚያዝያ 23 ለመረጣቸው የፊልም ባለሙያዎች ሽልማቶቹን አበርክቷል። ተሸላሚዎቹን አነጋግረናል።
ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት ሜዲትራኒያን ላይ ከደረሰው የመርከብ መገልበጥ አደጋ በመቶዎች የተቆጠሩ ፍልሰተኞች መሞታቸውን ወይም የደረሱበት አለመታወቁን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።ሊቢያ የሚገቡት በርካታ ስደተኞች ለተለያዩ አደጋዎች እንደሚጋለጡና በህገወጥ አዘዋዋሪዎች የሚደርስባቸው በደል አስከፊ እንደሆነ በጉዞው ያለፉ ስደተኞች ይገልፃሉ።በሊቢያ ይገኙበታል በተባለው ስልክ በመደወል ህገወጥ ደላሎቹን እንዲሁም በሊቢያ ታግተው የሚገኙ ስደተኞችን አነጋግረናል።
በእያንዳንዷ ቀን በሚልየን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በፕላስቲች ጠርሙሶች የታሸጉ የተጣራ ውሃን ጨምሮ የተለያዩ ጣፋጭ ፈሳሾችን ይጠቀማሉ። ከ60 ሚልየን በላይ የሚሆኑት እነዚህ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ከአገልግሎት በኃላ ይጣላሉ ወይም በየቀኑ ይቃጠላሉ። በቅርቡ ግን ሁለት ስራ ፈጣሪ ወጣቶች እነዚህን የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወደ ጫማነት በመቀየር አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እያደረጉ ነው።
ዛሬ የሰራተኞች ቀን በመላው አለም ተከብሮ ውሏል። በሃገራችንም ይህ ቀን መከበር ከጀመረ ከ 40 አመታት በላይ ተቆጥረዋል። በአለማችን የሚከበረው ይህ የሰራተኞች ቀን ዘንድሮ በኢትዮጵያ እንዴት ተከብሮ ዋለ? ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች በለፍ ተቀደም በመደወል ያገኘናቸው ጥቂት ነዋሪዎች የግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከ5 ሚልየን በላይ የሚሆኑ ያለ ስራና መኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎችን በ90 ቀናት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚያዝ አዋጅ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ዜጎችን በተመለከተ የባለስልጣናት ልዑካን ቡድን ወደ ሳውዲ አረቢያ በመላክ ከሚመለከታቸው ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት ጋር መክሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም የሰጡት አጭር ማብራሪያ።
በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በሕዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነትን ለማጠናከር በሚል በሙዚቃና ዳንስ የተቀነባበረ የልምድ ልውውጥ ተካሂዶ ነበር። መኖሪያቸው በዩናይትድ ስቴትስ ኒውዮርክ የሆኑት ዳንሰኞች ወደ አዲስ አበባ የደረሱት በዚሁ ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ፤ በምስራቅ አፍሪካ ምጣኔ ሃብትን በተመለከተና አሸባሪነትን ለማጥፋት በዋሽንግተን ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጋር ህብረት ለማጠንከር ነበር የተዘጋጀው።
የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሳውዲ አረቢያ በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንን ለመቀበልና አስፈላጊውን እርዳታ ለመስጠት የሚሰራ አዲስ ግብረሃይል እንዳቋቋመ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በሰጠው ማብራሪያ አስታውቋል። ምስሉ ከሶስት አመታት በፊት የተነሳና ከማህደራችን የወሰድነው መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
በሳውዲ አራቢያ ከ5 ሚልየን በላይ የሚሆኑ ያለ ስራና መኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ሰዎችን በ90 ቀናት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚያዘው አዋጅ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። ሳውዲ አረቢያን በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በስራ የተሰማሩ ሰዎች ይገኛሉ። ይወጣውን ህግ በተመለከተ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ይህ ህግ ከስድስቱ ሃገራት በሚመጡ ዜጎች ላይ ለ90 ቀናት የተቀመጠውን የቪዛ ፈቃድን የሚያግድ ሲሆን ኢራቅ ከታገዱት ስድስት ሃገሮች ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የአለም አቀፍ ስደተኞችን በማስመልከት የወጣው ውሳኔ 120 ቀናት እንዲቋረጥም ያዛል።
ለወራት ‘አፈቅርሻለሁ’ እያለ በየሄደችበት የሚከተላት፣ መውጪያ መግቢያ ያሳጣት የነበረ ወጣት አንገቷን በስለት ሁለት ቦታ ወግቶ ከመሬት እንደዘረራትና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተጯጩኸው ከወደቀችበት አፋፍሰው በአቅራቢያ ወደሚገኘው ባልቻ ሆስፒታል እንዳደረሷት፤ የፈሰሳት ደም ብዙ በመሆኑ በህክምና ህይወቷን ለማትረፍ ሳይቻል እንደቀረ እናቷ ወ/ሮ ወይንሸት ወዳጆ ይናገራሉ።
በተንቀሳቃሽ ምስሎች ቅንብር እና ለሲኒማና ለቲያትር ትዕይንት አስፈላጊ የገፅታ ለውጦች ለማድረግ በሚውል የጥበብ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነጥበብ ትምህርት ቤት የማዕረግ ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል። ተስፋዬ ወንድምአገኝ ስርየት፣ አሽንጌ፣ ጤዛ፣ አትሌቱ፣ ይፈለጋል እና በሌሎችም በበርካታ ፊልሞች ላይ የፊልም ጥበብ አሻራውን አሳርፏል። ተስፋዬ “ጥቁር ሰው” በተሰኘው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ የአድዋ ጦርነት ምን ይመስል እንደነበር በፊልም ጥበብ እንድናይ አስችሎናል።
ባሳለፍነው አርብ በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ግዛትና አካባቢዋ ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል የሃገሪቱ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው ነበር። ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘም በበርካታ የውጪ ሃገር ዜጎች ላይ ዝርፊያና ድብደባ ተፈፅሟል። ንብረታቸውን የተዘረፉ ኢትዮጵያውያንን አነጋግረናል።
በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ በዛሬው ዕለት በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የውጭ ዜጎች በተለይ ናይጄሪያውያን ከሃገራችን ይውጡ የሚሉ መልዕክቶች ሲስተጋቡ ውለዋል። ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ በተነሳው ረብሻ የውጭ ዜጎች የንግድ ተቋማት ተዘርፈዋል። ከተዘረፉት የንግድ ተቋማት ውስጥ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን እንደሆነ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ መሪ አቶ ታምሩ አበበ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ወደ ጣልያንና የግሪክ የባህር ወደብ የሚጎርፉ ስደተኞች ላይ የተሰሩ ሁለት ጥናታዊ ፊልሞች የዚህ አመት የኦስካር እጩ ሆነዋል። በ ጃንፍራንኮ ሮሲ የተዘጋጀው ፋየር አት ሲ “fire at sea” የተሰኘው ፊልም በረጅም ጥናታዊ ፊልም መደብ ፎር ፖይንት ዋን ማይልስ “4.1 Miles” የተሰኘው በዴልፊ ማትዚኣራኪ የተሰራው ፊልም በአጭር ጥናታዊ ፊልም መደብ እጩ ሆነው ቀርበዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ