ያለመኖሪያና ስራ ፈቃድ በሃገሪቱ የሚኖሩ ህገወጥ ዜጎች እንዲወጡ የሚያዘውን የጊዜ ገደብ በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቷል። ከቀናቶች በፊት የሳውዲ መንግስት በሃገሪቱ የተገኙትን ህገወጥ የሚላቸውን ስደተኞች በማሰር ላይ ይገኛል።
በዋሽንግተን ዲሲና አጎራባች ግዛቶች ቨርጂኒያ እና ሜሪላንድ ነዋሪ የሆኑ ቁጥራቸው ከ350 በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በጋራ የአጭር ርቀት ሩጫና የእግር ጉዞ ባሳለፍነው ቅዳሜ አካሂደዋል።
ህጋዊ የውጭ ሀገር ነዋሪዎችን የሚመለከት ክፍያ የሳዑዲ መንግስት ከሰኔ 24 ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል። በየወሩ አንድ መቶ ሪያል በነፍስ ወከፍ እንዲከፍሉ የሚያስገድደው ይህ ሕግ በየአመቱ እየጨመረ እንደሚሄድም ነው የተጠቀሰው። በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ሕጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደሃገር ለመመለስ የሚያስፈልጋቸው መሰረታዊ ነገሮች እንዲሟሉላቸው የኢትዮጵያ መንግስትን ጠይቀዋል።
በሜድትራያን በኩል ያለውን ፍልሰት ለተወሰኑ ወራቶች ለማቆም ስትል ጣልያን ከህገ-ወጥ የስደተኛ አሸጋጋሪዎች ጋር ለተያይያዙት ሊብያውያን ሚሊሻዎች ገንዘብ እየከፈለች ነው የሚል ክስ ቀርቦባታል። በፓሪሱ የአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ላይ በሜዲትራኒያን የሚገቡ ፍልሰተኞች ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶታል። ከዚህ ቀደም በሊቢያ በረሃ መጋዘን ውስጥ ታሽገናል ያሉን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትርውያን ስደተኞች አቅርበን ነበር። አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ የምጣኔ ሃብት፣ የስነሕዝብና የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ ነው። "መንገደኛ" የተሰኘ በደቡብ አፍሪካ የተወሰኑ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እውነተኛ ታሪክ የያዘ መጽሃፍ ባሳለፍነው አመት ለአንባብያን አበርክቷል። ዮርዳኖስ ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ ለወራት የሚሰሩትን እየሰራ፣ የሚበሉትን እየበላና ከሚያድሩበት አብሮ እያደረ የተመለከተውን ህይወታቸውን ነው በጽሁፍ ያሰፈረው።
ሶማሊያዊ- አሜሪካዊቷ ኢማን እ.አ.አ በ1970 እና 80ዎቹ ከነበሩት የፋሽን ሞዴሎች መካከል በጣም ቀልብ የምትስብ ሞዴል ነበረች። በቅርቡ ደግሞ ሌላይቷ ታዳጊ ሶማሌ-አሜሪካዊቷ ሞዴል ሂጃብ ለብሳ የጣልያንና የኒውዮርክ የፋሽን መድረኮች ላይ ለመታየት የመጀመሪያዋ ሆናለች፤ በተለያዩ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንም መነጋገሪያ ርዕስ ሆናለች።
በሊባኖስ ህጋዊ የስራ ፈቃዳቸው ወቅቱ አልፎበት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን መንገድ ለማመቻቸት በሁለቱ ሃገሮች መንግስታት በተደረገ ስምምነት መሰረት መመለስ ለሚፈልጉት ሁለተኛ ጉዞ ሊካሄድ ነው።
የስብዓዊ መብት ተሟጋች Human Rights Watch ትላንት ባወጣው መግለጫ ከትላንት በስትያ ሮም ከተማ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የጣልያን ፖሊስ ሃይል ባለው ውሃ ያደረሰው ጉዳትና ድብደባ መብት የጣሰ ነው፤ የጣልያን መንግስት ጉዳዩን በፍጥነትና በጥልቀት መመርመር አለበት ሲል አስታወቀ። ለስደተኞቹ አስቸኳይ መጠለያ እንዲያዘጋጅላቸውም የጣልያን መንግስትን ጠይቋል። ስደተኞቹ ውሎና አዳራቸው ምን ይመስላል? ትላንት ለቪኦኤ የሚገኙበትን ሁኔታ ገልፀዋል።
በጣልያን ሮም ከተማ በጥገኝነት ይኖሩ የነበሩ ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ለአራት አመታት ከኖሩበት በጣልያን ፖሊሶች ተገደው እንዲወጡ ተደረገ። ቅዳሜ አጥቢያ ላይ ነው በእንቅልፍ ላይ ሳሉ ነው በታጠቁ ፖሊሶች እየተዋከብቡ ጊዜያዊ መኖሪያቸውን እንዲለቁ የተገደዱት። ስደተኞቹ በሮማ ከተማ መንገድ ላይ መዋል ማደር ከጀመሩ ቀናቶች መቆጠራቸውንና መፍትሄው በመዘግየቱ ምክንያት ቅር መሰኘታቸውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ለአመታት በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየደረስ የሚገኘውን ፈተና ከመሰረቱ መፍትሔ ለማበጀትና መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና በህመም ምክንያት በየመጠለያው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ችግሮች ዙሪያ ነበር ውይይቱ።
ቤተሰብ መሥርተው ለብዙ ዓመታት ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በአዲሱ ክፍያ ንረት ምክንያት ቅሬታ እንዳላቸው ለቪኦኤ ገልፀዋል። ካለፈው ሐምሌ አሥር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የመጀመሪያው በወር የአንድ መቶ ሪያል የነፍስወከፍ የክፍያ ተመን በየዓመቱ በመቶ ሪያል እየጨመረ እንደሚሄድ ነው ደንቡ የደነገገው። በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሪያድ በሚገኘው የማኅበረሰብ ቢሯቸው አማካኝነት ተሰባስበው መፍትሄ ይሆናሉ ባሏቸው ሃሳቦች ላይ ተወያይተው ነበር።
በስፔን የሚዘጋጀው አመታዊ የአውሮፓ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል/ የሙዚቃ ዝግጅት/ ላይ ስምንት ኢትዮጵያዊ የሬጌ አቀንቃኞች እንዲዘፍኑ ተመረጡ። ሮቶ ቶም ሰንስፕላሽ /Rototom Sunsplash/ የተሰኘው ይህ የሙዚቃ ፌስቲቫል በነሃሴ ወር ነው የሚካሄደው። በዝግጅቱ ለመካፈል ከተመረጡት ሙዚቀኞች መካከል የተወሰኑትን በጋቢና ቪኦኤ የሬድዮ ዝግጅታችን ጋብዘን ነበር።
ባሳለፍነው ወር መጨረሻ በዛንዚባር በተዘጋጀው ዚፍ /ZIff/ በተሰኘው የአፍሪካ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊ ፊልሞች ለውድድር ቀርበው ነበር። በአጭር የፊልም ዘርፍ የማንተጋፍቶት ስለሺ "ግርታ" እና በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ የተሰራውና በሰሎሜ ሙሉጌታ የተዘጋጀው "ዉቭን" በአማርኛው የተሸመነ የተሰኘው ወጥ ሙሉ ፊልም ከሌሎች የአፍሪካ ፊልሞች ጋር በዘርፉ ባለሙያዎች ለመታየት በቅቷል። ከአጭር የፊልም ዘርፍም "ግርታ" ተሸላሚ ሆኗል። አዘጋጆቹን አነጋግረናል።
ተመስገን ያሬድ ይባላል። ከዚህ ቀደም ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ነጠላ ዜማዎችንና ሙሉ አልበሞችን ለአድማጭ አበርክቷል። በቅርቡም ‘ሊሎ ‘ የተሰኘ ነባር የትግሪኛ ነጠላ ዜማ በአዲስ ቅንብር በማዜም ተወዳጅ ሆኗል። በማህበራዊ ደረ ገፆች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሶስት ሚልየን በላይ የሙዚቃ አድናቂዎች ተጎብኝቶለታል፤ ተደምጦለታል።በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት እየዞረ በማቀንቀንም ለሙዚቃ አድናቂዎቹ ብቃቱን እያስመሰከረ ይገኛል። አማርኛ ትንሽ ከመስማት ውጭ መናገር አይችልም።
በርካታ ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነዳቸውን ጨርሰው የአውሮፕላን ትኬት ቢቆርጡም በአውሮፕላን በረራ እጥረት ምክንያት ሲጉላሉ ከርመዋል። ዛሬ የሳውዲ ተጨማሪ አውሮፕላኖች በሳውዲ መንግስት በመፈቀዱ ከሳውዲ ሪያድ በርካቶች ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ እንደጀመሩ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ መሪ አቶ ሻውል ጌታሁን ለቪኦኤ ገልጸዋል። በርካታ ተመላሾች በሪያድ አውሮፕላን ጣቢያ ተራ እስኪደርሳቸው በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም አክለው ተናግረዋል።
ከኢድ በዓል ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የጉዞ ሂደት መጨናነቅ ምክንያት ቀነ ገደቡ እንደተራዘመና የኢትዮጵያ መንግስት ላቀረበው የቀን ጥያቄ ጭማሪ ምላሽም ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ለቪኦኤ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ቆርጠው መሳፈር ያልቻሉ ተመላሾች ዛሬም ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ መሪ አቶ ሻውል ጌታሁን ቢሮው ባዘጋጃቸው መጠለያ ውስጥ ስለሚገኙት ተጓዞች ሁኔታ ይገልፃሉ።
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ የመጨረሻው ሳምንት ምን ይመስል ነበር? ከሪያድ ከተማ የምዝገባ ጣቢያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ መሪ /ኃላፊ/ አቶ ሻውል ጌታሁንን አነጋግረን ነበር። ይህ መረጃ የተሰጠን ከቀናቶች በፊት ነው። 60ሺህ የነበረው የተመዝጋቢ ቁጥር በመጨረሻዎቹ ቀናት ከ80ሺህ በልጧል። ይኖራሉ ተብለው ከሚገመቱት 400 ሺህ ገደማ ከሚደርሱት ፈቃድ ከሌላቸው ኢትዮጵያውያን ጋር ሲነጻፀር አሁንም የተመዘገበው ተመላሽ ቁጥር አነስተኛ ነው። ለድምጽ ጥራቱ ይቅርታ እንጠይቃለን።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች መንግስታት የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ እንዲራዘም ቢጠይቁም ከሳውዲ መንግስት የተሰጠ ምላሽ የለም። የኢ/ አየር መንገድ ከተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ሳምንታዊ የበረራ ቁጥሩን ለማሳደግ ጥረት ቢያደርግም በሳውዲ አቪየሽን ፈቃድ ያገኘው ለተጨማሪ 17 በረራዎች ብቻ መሆኑን ከድርጅቱ ተረድተናል። በርካታ ተመላሾች በአውሮፕላን ትኬትና በበረራ እጥረት ምክንያት እየተንገላቱ እንደሆነ ይናገራሉ።
የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ሠራተኞች ወደየሀገራቸው እንዲመለሱ ያወጣው የ90 ቀናት ጊዜ ገደብ 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል። ለመመለስ የማይፈልጉ ኢትዮጵያዊያንም ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ “የሚመጣውን ለመቀበል” ዝግጁ ነን ሲሉ አስረድተዋል። የጉዞ ሰነድ ባለመውሰዳቸው በሪያድ አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች በሳውዲ ፖሊስ መታሰራቸውን የገለጹ፤ ወደ ሰማንያ እንሆናለን ብለዋል፤ ሽመንስ በተባለ እስርቤት የድረሱልን ጥሪያቸውን አሰምተዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ