እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም 7500 በላይ የፆታ ንግድ እየተካሄደ እንደሚገኝ ድርጊቱን ለመከላከል በዩናይትድ ስቴትስ ለተቋቋመው ድርጅት መረጃ ደርሷል። በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ በመካከለኛውና በዝቅተኛ ገቢ ከሚተዳደሩ ቤተሰብ የሚገኙ አዳጊ ሴት ልጆችን በመከታተልና በቁሳቁስ በመደለል እንደሚያጠምዱዋቸው ነው መረጃው የሚያሳየው። የአሜሪካ ድምፅ ባልደረባችን ካሮላይን ፐርሱት ከፖሊሶች ምርመራ ጋር አብራ በመጓዝ ያደረሰችን ዘገባ ነው። የመጀመሪያው ክፍል እነሆ!
አንጋፋው ተዋናይ ፈቃዱ ተ/ማሪያም ከስኳር ህምም ጋር በተያያዘ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልገው ተነግሯል።የሙያ አጋሮቹ ለህክምና የሚውለውን ወጪ ለማሰባሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ከቀናት በፊትም የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የፈቃዱ ተ/ማርያምን የህክምና ወጪ ለመሸፈን ቃል ገብቷል። የሙያ አጋሮቹ በተገባው ቃል ላይ ምን ይላሉ? የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ለፈቃዱ ተ/ማሪያም ነፃ ህክምና የሰጠበት ምክንያትስ ምንድነው?ዴኤታው ይመልሳሉ።
በሀዋሳ የአዋዳ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ናት።
ለአንጋፋው ተዋናይ ፈቃዱ ተክለማሪያም ለበርካታ ተዋንያን አረያና ደጋፊ እንደሆነ ይመሰከርለታል። በቅርቡ በደረሰበት የጤና መታወክ ምክንያት ለሚያስፈልገው ህክምና የሚውል ንዘብ የሚያሰባስብ ግብረሃይል ዛረ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ፈቃዱ ጤንነቱን በራሱ አንደበት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዬ ተናግሯል።
ወ/ሮ አትክልት ጂያንካ በሆስፒታልና በተለያዩ ቦታዎች ተጥለው የተገኙ በርካታ ህፃናትን በማሳደግ ነው የሚታወቁት።
በኢትዮጵያ የቅርብ ሴት ጓደኛማቾች በጋራ የመሰረቱት “safe house” በአማርኛ "ከለላ ቤት" የተሰኘው የግብረሰናይ ድርጅት የተጎዱ ሴቶች የሚያገግሙበት መጠለያ ነው።
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የነበሩና ትምህርታቸውን በሀንጋሪ በመከታተል ላይ የሚገኙ ሰላሳ የሚሆኑ ተማሪዎች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለችግር እንደተጋለጡ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገለፁ።
በርካታ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሃገር ዜጎች በተገኙበት ኢትዮጵያዊ የባህል ዝግጅት በዋሽንግተን ዲሲ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ተካሂዶ ነበር።
ስደተኞችን የሚመለከተውን የእስራኤልን ህግ በመቃወም ከሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች በቴላቪቭ አቅራቢያ ቅዳሜ ምሽት ለሶስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ወደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በ3 ወር ጊዜ እስራኤልን ለቀው እንዲወጡ ሃገሪቱ ትዕዛዝ ካስተላለፈች 2 ወራት ተቆጥረዋል።በእስራኤል ሆሎት የስደተኛ ማቆያ ጣቢያ ከሚገኙት ኤርትራውያን ስደተኞች መካከል አንዱ ተከስተ የማነህ ስለሰላማዊ ሰልፉ በአጭሩ ገልጾልናል ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝን የስልጣን መልቀቅ ጥያቄን ተከትሎ ሰዎች የሰጡት ጥቂት አስተያየቶች
“Yellow Movement” ወይም "የቢጫ እንቅስቃሴ “ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎችን ለማጠንከር የዛሬ ሰባት አመት ነው የተመሰረተው። ከ35 በላይ አባላትም አሉት።
ፊልሙ የተሰራው በጀርመናዊቷ የፊልም ተማሪ ሲሆን፤ እ.አ.አ. በ 2015 ዓ.ም ከናይሮቢ ማንዴራ ወደተባለች የኬንያ አንዲት ግዛት ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የደረሰበትን የአሸባሪዎች ጥቃት ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ ነው። ይህ ፊልም ለዘንድሮው የሆሊውዱ የኦስካር ሽልማት እጩ ከሆኑት ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው።
ሄርዘሊያ በተባለችው የእስራኤል ከተማ በተደረገው በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥገኝነት የጠየቁ በርካታ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ መጡበት ሃገር ወይም ስደተኞቹን ለመቀበል ወደተስማሙ ሁለት የአፍሪካ ሃገሮች /ሩዋንዳና ኡጋንዳ/ በ3ወር የጊዜ ገደብ እንዲሄዱ የእስራኤል መንግስት ወስኗል። ካልሆነ ግን ስደተኞቹ ለእስር ይዳረጋሉ። ተከስተ የማነ ከኤርትራውያን ስደተኞቹ መካከል አንዱ ነው።
በአርቲስት ተስፋዬ ንጉሴ የተሳሉት የቀለም ስዕል ስራዎች በዩናይትድ ስቴትስ የጥበበኞች ከተማ በሆነችው ኒው ኦርሊየንስ ለዕይታ ሊቀርቡ ነው። በዚህ በያዝነው ወር አጋማሽ በሺዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍ የጥበብ ባለሙያዎችና አድናቂዎች በስዕል ኤግዚቢሽኑ ላይ ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመቶሺዎች የሚገመቱ በቤሩት ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን መካከል ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባሉት ያለስራና መኖሪያ ፈቃድ በስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
ተከስተ የማነ ከሰባት ዓመት በፊት ሀገሩን ኤርትራን ለቆ የሊቢያ በረሃን አቋርጦ እስራኤል የገባው በፖለቲካ ስደት ምክንያት እንደሆነ ይናገራል።
የአባ ሙሴ ዘርዓይ ስም የሊቢያን በረሃና የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን ለሚገቡ ስደተኞች በተለይም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስደተኞች ትልቅ ዋጋ አለው።
የአለም አቀፉ የፍልሰት ቀን ትላንት ተከብሮ ውሏል። በኢትዮጵያም በአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት IOM አማካኝነት ለአንድ ሳምንት ስደተኞችን በሚመለከቱ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ነበር ።
በጣሊያን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ለአራት ዓመታት ከኖሩበት ህንፃ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለፈው የነሃሴ ወር በጣልያን ፖሊሶች ተገደው እንዲወጡ መደረጋቸውን ዘግበን ነበር። በጊዜው የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት የሳበው የእነኚህ ተፈናቃይ ስደተኞች ጉዳይ “ለመሆኑ እንደምን ካለ እልባት ላይ ደረሰ?” ስንል ወደ ስደተኞቹ ደውለን ነበር።
በቤሩት በቤት ውስጥ ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች ወጣት ባልና ሚስት አስሪዎቿ ላይ አደጋ አደረሰች በሚል ተከሳ ፍርድ ቤት ቀርባለች።
ተጨማሪ ይጫኑ