ሰማያዊ ፓርቲ አንዳንድ የአመራር አባላቱና ተራ አባላቱ አሁንም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በፀጥታ ኃይሎች እየታሰሩብኝ ናቸው ሲል አማረረ፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ የደረሱበት አይታወቅም ብሏል፡፡
በቀድሞ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር በአቶ በቀለ ገረባ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የሲዲ ወይንም የድምፅ ከምስል ማስረጃ ዛሬም በቴክኒክ ችግር ምክንያት ሊታይም፣ ሊደመጥም እንዳልቻለ ተገለፀ፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቀደም በለው በሰየሙትና በተወካዮች ምክር ቤት ባለሞያዎች አማካኝነት በቀረበላቸው የክርክር እና የድርድር የአሰራር ረቂቅ ደንብ ላይ ለመወያየት ሌላ ቀጠሮ ተለዋወጡ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ አድርገዋል በሚልና ከአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ርምጃዎች ጋራ የተያያዙ ግዴታዎችን በመተላለፍ ወንጀል በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ክስ መሠረተ። ከእርሳቸው ጋርም በዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በጀዋር መሐመድ ላይም ተመሣሣይ ክስ መሥርቷል።
የፌደራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል ለምስክርነት የተፈለጉትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን ለአራተኛ ጊዜ ሳያቀርባቸው ቀረ፡፡
የሚጠበቀው ድርድር በሕዝብና በተደራዳሪ ፓርቲዎች እምነት አንዲጣልበት በድርድሩ ላይ ያገባኛል የሚል ወገኖች ሁሉ መንግሥት በሩን ክፍት እንዲያደርግ ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ፡፡
“ሜንሽን ፊዩር ሜንሽን” ወይንም “ሰዎች ለሰዎች” የተሰኘው ግብረ ሠናይ ድርጅት እ አ አ በ2017 በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው የተለያዩ መረሃ ግብሮች ከ2 መቶ ዘጠና ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መያዙን ይፋ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት በነበረው መደበኛ ስብሰባው ሰማያዊ ፓርቲ ከአምስት ወራት በፊት ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ ተቀብሎ ዕውቅና መስጠቱን አመለከተ፡፡
እነ መብራቱ ጌታሁን በሚል መዝገብ የሽብር የክስ ሽብር የተመሰረተባቸው የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አምስት የኮሚቴ አባላት የክስ መቃወሚያ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገባቸው፡፡
ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግና ተደራዳሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ ሰባት አባላት ባለው ኮሚቴ በሚዘጋጅ የጋራ መነሻ ሃሳብ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡
በሽብር አድራጎት የተከሰሱት እነ ንግሥት ይርጋ ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ መልስ መስጠት እንዳልቻ ፌደራል አቃቤ ሕግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልክቶ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቆች ተቃውመዋል።
የጀርመን ድምፅ (ዶይቸ ቬለ) ጋዜጠኛ ለሥራ በሄደበት አፋር ክልል ለሰዓታት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ተፈትቷል፡፡
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በኢንተርቴት አምደኞቹ በእነ ሶሊያና ሽመልስና በአቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ውሳኔ ለመስጠት መዝገቡን ለሰባተኛ ጊዜ ቀጠረ፡፡
በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግና በሃገር አቀፍ ተቃዋሚዎች ፓርቲዎች መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ላይ፤ ድርድሩ የሚካሄድበትን የሥነ ስርዓት አማራጭ ሃሳብ ስድስት ተቃዋሚዎች ፓርቲዎች ለመንግሥት ማስገባታቸውን አስታወቁ፡፡
የአዳማው ሎጂስቲክ ሃብ (የማጓጓዣና ስርጭት ማዕከል) በዓለም የምግብ ድርጅትና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ አማካኝነት ተስፋፍቶ በመታደሱ አቅሙና ቅልጥፈናው ከፍ ማለቱ ተመለከተ፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የደህንነት ኮሚሽነር በሊቢያ ያለው ሁኔታ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን አመልከተ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ለመመለስ ዛሬ ያወሰደችው እርምጃ ለአህጉሪቱ ሕብረትና እርስ በርስ መረዳዳት አንድ ትልቅ ፈተና ደቅኗል ሲሉ ተሰናባቿ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ላሚኒ ዙማ አሳስበዋል፡፡
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኢንተርኔት አምደኞች በነሶሊያና ሽመልስና በአቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ለስድስተኛ ጊዜ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡
ፖሊስ ለሦስተኛ ጊዜ በዶ/ር መረራ ጉዲና ጉዳይ ላይ የ28 ቀናት የምርምራ ጊዜ ተሰጠው፡፡ ጠበቆቻቸው የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትም ማመልከቻም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
“ይካሄዳል” በሚባለው የገዥው ኢህአዴግና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርድር ዙሪያ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ላይ መረጃ ለጠየቀው በኢትዮጵያ የኖርዌይ ኤምባሲ ሰማያዊ ፓርቲ የበኩሉን ማስታወቁን አመልክቷል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ