አዲስ አበባ —
እነ መብራቱ ጌታሁን በሚል መዝገብ የሽብር የክስ ሽብር የተመሰረተባቸው የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አምስት የኮሚቴ አባላት የክስ መቃወሚያ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገባቸው፡፡ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራክረዋል፡፡ አቃቤ ሕግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥቷል፡፡
ቀደም ሲል የፌደራል አቃቤ ሕግ እነ መብራቱ ጌታሁን በሚል የክስ መዝገብ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባልነት ከሚታወቁት መካከል በመብራቱ ጌታሁን፣ አታላይ ዛፌ፣ ጌታቸው አደመ፣ አለነ ሻማና ነጋ ባንቲሁን ላይ የአሸባሪነት ክስ መስርቶባቸዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ