በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእነ ንግሥት ይርጋ ጉዳይ እንደገና ተቀጠረ


በሽብር አድራጎት የተከሰሱት እነ ንግሥት ይርጋ ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ መልስ መስጠት እንዳልቻ ፌደራል አቃቤ ሕግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልክቶ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቆች ተቃውመዋል።

በሽብር አድራጎት የተከሰሱት እነ ንግሥት ይርጋ ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ መልስ መስጠት እንዳልቻለ ፌደራል አቃቤ ሕግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልክቶ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቆች ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ሕግ ጥያቄ ምክኒያታዊ ነው ሲል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፌደራል አቃቤ ሕግ ታኅሥስ 28/2009 ዓ.ም በንግሥት ይርጋ፣ በአለምነህ ዋሴ፣ በቴዎድሮስ ተላይ፣ በአወቀ አባተ፣ በበላይነህ አለምነህ እና በያሬድ ግርማ ላይ በመሠረተው ክስ "ተከሳሾቹ አርበኞች ግንቦት ሰባት ብሎ እራሱን ከሚጠራው የሽብር ቡድን ከፍተኛ አመራር አባላት፣ ውጭ ሃገር ከሚገኙ እንዲሁም ሀገር ውስጥ ከሚገኙ፣ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ከታጠቁ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ተልዕኮ በመቀበል በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አመፅ በማስነሳት፣ አመፁን በመምራትና በማስተባበር የሽብርተኝነት ድርጊት ፈፅመዋል" ብሏ ል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የእነ ንግሥት ይርጋ ጉዳይ እንደገና ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG