አዲስ አበባ —
ሰማያዊ ፓርቲ አንዳንድ የአመራር አባላቱና ተራ አባላቱ አሁንም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በፀጥታ ኃይሎች እየታሰሩብኝ ናቸው ሲል አማረረ፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ የደረሱበት አይታወቅም ብሏል፡፡
ድርጊቱ በተቃዋሚዎችና በገዥው ፓርቲ መካከል በሚካሄድው የቅድመ ድርድር ዝግጅት ላይ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አስታወቁ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ተሰማ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስታወቁት ከየካቲት ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ አባሎቹና ጥቂት የፓርቲው አመራር አባሎችም በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እየዋሉ ይገኛሉ፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ