በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ቡሩንዳውያንና ከአገሪቱ የተሰደዱ የህዝባዊ ማህበራት መሪዎች የሰብአዊ መብት ረገጣው እንደተባባሰ ገልጸዋል


በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ቡሩንዳውያና ከአገሪቱ የተሰደዱ የህዝባዊ ማህበራት መሪዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት አከባቢ ሰልፍ አካሂደዋል። የቡሩንዲ የድህረ-ምርጫ ግጭት ሁለተኛ አመቱን በያዘበት በአሁኑ ወቅት የመንግስታቱ ድርጅት የሀገሪቱን ህዝብ የሚጠብቅ የፖሊስ ሃይል እንዲልክ ሰልፈኞቹ ተማጽነዋል።

በመንግስታቱ ድርጅት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ሆነው የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት ቡሩንዳውያን በሀገራቸው ያለው ሁኔታ እየከፋ በሄደበት በአሁኑ ወቅት የሰብአዊ መብት ረገጣው እየተባባሰ ነው ብለዋል። ሳንድራ ባራንሲራ በካናዳ ያሉት ቡሩንዳውያን ህበረትን ወክለው ተናግረዋል።

“ሁላችንም አብረን መቆም አለብን። ይህ የቡሩንዲና የአፍሪቃ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የስብእና ጉዳይ ነው።”ብለዋል።

የቡሩንዲ ፕረዚዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ የስልጣን ጊዜ እንደሚወዳደሩ ባለፈው አመት ካስታወቁበት ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱ በተከታታይ ግጭቶች ስትታመስ ቆይታለች። ፕረዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ በስልጣን መቀጠላቸው ህገ-ወጥ ነው ይላሉ ተቃዋሚዎቹ።

ፕረዚዳንት ንኩሪንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ከተመረጡ ወዲህ በቀጠለው ግጭት 700 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ታስረዋል። ግጭቱ ይፈነዳል የሚል ስጋትም አለ። ሳንድራ ባራሲራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን ጉዳይ መገንዘብ አለበት ይላሉ።

“ይህ ሁኔታ በቀላሉ ወደ ክልላዊ ጦርነት ሊለወጥ ይችላል። የመንግስታቱ ድርጅት ይህን መገንዘብ ይኖርበታል።”ብለዋል።

ፕየር ክላቨር ምቦኒምፓ የተባሉ የሰብ-አዊ መብት ታጋይ ግድያ በተሞክረባቸው ወቅጥ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

“አለም አቀፍ ህብረተሰብ ማለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት ቡሩንዱ ገብተው ህዝቡን እንዲጠብቁ ጠይቀናል።”ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን ባለፈው የካቲት ወር ቡጁምቡራን ጎብኝተው ሀገሪቱን በማረጋጋት ተግባር የሚረዳ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፖሊስ ሃይል እንዲላክ ምክረ-ሃሳብ አቅርበዋል።

የሚላኩት ፖሊሲች 3,000 እንዲሆኑ ወይም ደግሞ ጥቂት ያልታጠቁ የፖሊስ አማካሪዎች እንዲላኩ ነው እንደ አማራጭ ሃሳብ የቀረበው። የእንኩሪንዚዛ መንግስት ግን ማንኛውንም አይነት የታጠቀ አለም አቀፍ ሀይል እንዲላክ እንደማፈልግ ግልጽ አድርጓል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ስለ ሚላከው ሃይል መጠንም ሆነ ስለ ሚያከነውናቸው ተግባሮች የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል።

ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት ፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት ቡሩንዳውያን የጸጥታው ምክር ቤት ቡሩንዲ ውስጥ የሚታየውን የደም መፋሰስ ተግባር ለማቆም ፈጣን ውሳኔ እንዲወሰድ ጥሪ አድርገዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬዮ ዘጋቢ ማርግሬት በሽር ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርበዋለች፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG