በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡሩንዲ ሰኞ ማታ ታጣቂዎች በአንድ ገበያ ውስጥ ተኩስ ከፍተው ቢያንስ አምስት ሰዎች ገደሉ


ፉይል ፎቶ - የብሩንዲ ፖሊሶች በቡጁምቡራ የተቃዋሚዎችን ሰልፍ እየበተኑ እ.አ.አ.
ፉይል ፎቶ - የብሩንዲ ፖሊሶች በቡጁምቡራ የተቃዋሚዎችን ሰልፍ እየበተኑ እ.አ.አ.

የምስራቅዋ ጊሱሩ ከተማ ነዋሪዎች ሲናገሩ ሰባት ወንጀለኞች ገበያው ውስጥ እየሮጡ ከተኮሱ በኋላ አምልጠዋል ብለዋል።

ቡሩንዲ ውስጥ ትናንት ሰኞ ማታ ታጣቂዎች በአንድ ገበያ ውስጥ ተኩስ ከፍተው ቢያንስ አምስት ሰዎች ገደሉ ሌሎች ስድስት ሰዎች አቆሰሉ ሲሉ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናገሩ።

የምስራቅዋ ጊሱሩ ከተማ ነዋሪዎች ሲናገሩ ሰባት ወንጀለኞች ገበያው ውስጥ እየሮጡ ከተኮሱ በኋላ አምልጠዋል ብለዋል።

አምስት ሰዎች መታሰራቸውን ለቪኦኤ የገለጡት የሪዩጉ ክፍለ ሀገር ባለልሥልጣን ሌሎች ተጠርታሪዎች ደግሞ በታንዜንያ አቅጣጫ ሸሽተው አምልጠዋል ብለዋል።

በደቡቧ ሙሳጋ ከተማም ትናንት ማታ ተኩስ መሰማቱ የተገለጠ ሲሆን ለጥያቄ የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ ተጠቁሟል።

ፕሬዚደንት ፒየር ኑኩሩዚዛ /ፋይል ፎቶ/
ፕሬዚደንት ፒየር ኑኩሩዚዛ /ፋይል ፎቶ/

ማንነታቸው ያልታወቀው አጥቂዎች ታንዜንያ ውስጥ ከሚገኙ በአንድ የቀድሞ ፕሬዚደንታዊ ቃል አቀባይ የሚመሩ ስደተኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ናቸው ተብሎ ይጠረጠራል። ቃል አቀባዩ ፕሬዚደንት ፒየር ኑኩሩዚዛን ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ባይወዳደሩ ይሻላል ብለው በማማከራቸው ባለፈው ዓመት ከስራ የተባረሩት ናቸው።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG