በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ መንግስት በቅርቡ ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረም ገልጿል


ፋይል ፎቶ - የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አላን ኒያሚትዌ
ፋይል ፎቶ - የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አላን ኒያሚትዌ

የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አላን ኒያሚትዌ መንግስታቸው በፀጥታ ሐይሎችና በደጋፊዎቹ አማካኝነት የተቃዋሚዎችን መብት ይጥሳል ተብሎ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የቀረበውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል።

የተቃዋሚዎችን መብት በመጣስ የሚወጀነለው የቡሩንዲ መንግስት በቅርቡ ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረም ተገለጠ።

የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አላን ኒያሚትዌ መንግስታቸው በፀጥታ ሐይሎችና በደጋፊዎቹ አማካኝነት የተቃዋሚዎችን መብት ይጥሳል ተብሎ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የቀረበውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል። የቡሩንዲ አስተዳደር ባሁኑ ጊዜ ጉዳዩን ለመመርመር ቡጁምቡራ ከሚገኙት የአፍሪካ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር እየተባበረ ነው ብለዋል።

የቀድሞ የሩዋንዳ አምባሳደር ዣክ ቢሆዛጋራ (Jacques Bihozagara) በቅርቡ ቡጁምቡራ በሚገኝ እስር ቤት መሞታቸውን ተከትሎ ተቃዋሚ ቡድኖች የቡሩንዲው መንግስት የዜጎችን መብት እየጣሰ ነው ሲሉ ከሰዋል።

ፋይል ፎቶ - የቀድሞ የሩዋንዳ አምባሳደር ዣክ ቢሆዛጋራ (Jacques Bihozagara)
ፋይል ፎቶ - የቀድሞ የሩዋንዳ አምባሳደር ዣክ ቢሆዛጋራ (Jacques Bihozagara)

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የቀድሞውን የሩዋንዳ አምባሳደር ሞት አስመልክቶ ምርመራ እንዲያካሂድ ተቃዋሚዎች ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ፕረዘደንት ባራክ ኦባማ ለብሩንዲ ህዝብ ከዚህ በፊት ያስተላለፉት መንእክት መዘገባችንም ይታወሳል። መልእክቱን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ መልእክት ለብሩንዲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00

XS
SM
MD
LG