በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ መንግስት የተ.መ.ድ የጸጥታ ካውንስል ያሳለፈውን 2279 ውሳኔ በበጎ መንፈስ እንደሚቀበል ገልጿል

ውሳኔው በቡሩንዲ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ የሚከታተል የመንግስታቱ ድርጅት የፖሊስ ቡድን እንዲመደብ ጥሪ ያደርጋል። ባለፈው አርብ የተወሰደው ውሳኔ ሁሉም ወገኖች ሀይል ተጠቃሚነትን እንዲያስወግዱና ጥላቻን የሚቀሰቅሱ አነጋገሮችን በይፋ ከማስማት እንዲቆጠቡ ጥሪ ያደርጋል።

የቡሩንዲ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ካውንስል ያሳለፈውን 2279 ውሳኔን በበጎ መንፈስ እንደሚቀበል ገልጿል።

ውሳኔው በቡሩንዲ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ የሚከታተል የመንግስታቱ ድርጅት የፖሊስ ቡድን እንዲመደብ ጥሪ ያደርጋል። ባለፈው አርብ የተወሰደው ውሳኔ ሁሉም ወገኖች ሀይል ተጠቃሚነትን እንዲያስወግዱና ጥላቻን የሚቀሰቅሱ አነጋገሮችን በይፋ ከማስማት እንዲቆጠቡ ጥሪ ያደርጋል።

የቡሩንዲ መንግስት ለሁሉም ዜጎች የመሰረታዊ ነጻነት ዋስትና እንዲሰጥም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ውሳኔ አሳስቧል። የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤለይን ኒያሚትዌ የፕረዚዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ መንግስት ምን ጊዜም ቢሆን በሀገሪቱ የአለም አቀፍ ህልውናን ይቀበላል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወታደሮች እስካልሆኑ ድረስ የድርጅቱ የፖሊስ ሀይል መመደቡንም በበጎ ይቀበላል ብለዋል። “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ካውንስል ውሳኔ የሚለው የፖሊስ ሃይልን ሳይሆን የፖሊስ አስተዋጾን ይልመስለኛል። እኛ የምንቃወመው የወታደሮች ምደባን በመሆኑ የፖሊሶች መመደቡ ሃሳብ የቡሩንዲን ጥቅም የሚጸረር አይመስለኝም” ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

ከለፈው ሚያዝይ ወር አንስቶ ከሁለት መቶ አምሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ከሀገሪቱ ተሰደዋል። ስፍር ቁጥር የሌላቸው ደግሞ በአገር ውስጥ ከመኖርያቸው ተፈናቅለዋል።

XS
SM
MD
LG