ዋሽንግተን ዲሲ —
"የሩዋንዳ መንግሥት ቡሩንዲ ውስጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እያሰናከለ ነው" ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችው ክስ፣ እኛን ነፃ ያወጣናል በማለት ቡሩንዲ አስታወቀች።
"ሩዋንዳ የሚገኙ የቡሩንዲ ስደተኞች፣ የቡሩንዲን መንግሥት እንዲወጉ ለትጥቅ ትግል ስለመመልመላቸው ተጨባጭ መረጃዎች አሉን" በማለት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪን-ፊልድ ትናንት ለምክር ቤቱ የውጪ ጉዳዮች ኰሚቴ ቃላቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።
ቡሩንዲ በዚህ ጉዳይ ለወራት ያህል ስትጮ የሰማት አልነበረምየቡሩንዲው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አልየን ንያማትዌ
"ቡሩንዲ በዚህ ጉዳይ ለወራት ያህል ስትጮ የሰማት አልነበረም" ያሉት የቡሩንዲው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አልየን ንያማትዌ(Alain Nyamitwe) "የሩዋንዳ የእስከዛሬ አካሄድ ከዓለማቀፉ ማኅበረሰብ አካሄድ ጋር ተቃራኒ መሆኑ ስለታወቀ፣ ከእንግዲህ ያለው ቀሪ ሥራና ተጨባጭ እርጃም የመውሰዱ ተግባር የዩናይትድ ስቴትስ ይሆናል» ብለዋል።