በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ መንግስት በደቡብ አፍሪቃ የሚቀርብ ሃሣብ በበጎ መንፈስ እንደሚቀበል ገልጿል


እአአ ባለፈው ጥር ስድስት ቀን በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ እንዲቀጥል ታቅዶ የነበረው ንግግር አልተካሄደም።

በቡሩንዲያውያን መካከል የሚካሄደውን ንግግር ለማስተባበር ከደቡብ አፍሪቃ የሚቀርብ ማንኛውንም አይነት ሃሣብ በበጎ መንፈስ እንደሚቀበል የቡሩንዲ መንግስት ገልጿል።

ከደቡብ አፍሪቃ የቀረበ ኦፊሴላዊ ሃሣብ ባይኖርም ሃሣቡ ከቀረበ የሀገሪቱ መንግስት እንደሚቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሉየን ንያማትዌ (Alain Nyamitwe) ተናግረዋል።

እአአ ከ1990 ዎቹ መጨረሻ እስከ 2000 ዎቹ መጀመርያ አመታት በነበረው ጊዜ ቡሩንዲ ውስጥ በተካሄደው የሰላም ሂደት ደቡብ አፍሪቃ ወሳኝ ሚና እንደተጫወተች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

በኡጋንዳው ፕረዚዳንት ዮወሪ ሙሴቬኒ መሪነት በምስራቅ አፍሪቃ ሸምጋይነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር እስካሁን ባለው ጊዜ ውጤት አልተገኘበትም። እአአ ባለፈው ጥር ስድስት ቀን በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ እንዲቀጥል ታቅዶ የነበረው ንግግር አልተካሄደም።

ሸምጋዮቹ ቀኑን የወሰኑት ከቡሩንዲ መንግስት ጋር ሳይመካከሩ ነው በማለት የሀገሪቱ መንግስት አልተቀበለውም።

XS
SM
MD
LG