በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከቡሩንዲ የሚሰደዱ የአገሪቱ ዜጎች 250,000 መድረሱን የተ.መ.ድ. አሳወቀ


ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መሥሪያ ቤት ቃል-አቀባይ መሊሳ ፍለሚንግ
ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መሥሪያ ቤት ቃል-አቀባይ መሊሳ ፍለሚንግ

ቡሩንዲ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነትና ፖለቲካዊ አመጽ ሽሽት የሚሰደዱ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር 250,000 መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መሥሪያ ቤት ቃል-አቀባይ መሊሳ ፍለሚንግ ገለጹ።

ቡሩንዲ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነትና ፖለቲካዊ አመጽ ሽሽት የሚሰደዱ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር 250,000 መድረሱን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መሥሪያ ቤት አሳወቀ።

ቃል-አቀባይዋ መሊሳ ፍለሚንግ ዛሬ ዐርብ እንዳስታወቁት፣ ፍልሰተኞቹን በሚያስተናግዱ አገሮች የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ከሚገባቸው በላይ ተጨናንቀዋል።

ለአብነትም፣ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ከ130,000 በላይ ቡሩንዲያውያን ፍልሰተኞችን የተቀበለችው የታንዛኒያ ተጠቅሳለች። መሊሳ ፍለሚንግ እንዳሉት ከሆነ፣ ለቡሩንዲው የስደተኞች ቀውስ ከተጠየቀው $175 ሚልዮን ውስጥ፣ መሥሪያ ቤታቸው የደረሰው 3%ው ብቻ ነው።

ከብሩንዲ የተሰደዱ ህፃናት
ከብሩንዲ የተሰደዱ ህፃናት

ቡሩንዲያውያን አገራቸውን እየተዉ መሸሽ የጀመሩት፣ ፕሬዚደንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ለሦሰኛ ጊዜ እወዳደራለሁ ብለው ይፋ ካደረጉና በዚያው "አወዛጋቢ" በተባለው ምርጫም ካሸነፉ በኋላ ነው።

የብሩንዲ ፕሬዚደንት
የብሩንዲ ፕሬዚደንት

በወቅቱ ምርጫው አወዛጋቢ የሆነው፣ ንኩሩንዚዛ ለሦስተኛ ጊዜ መወዳደራቸው "ህገ-መንግሥታዊ አይደለም" በሚል መሆኑም ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG