በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡሩንዲ መንግስታና በተቃዋሚዎች መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር እንዲዘገይ ተደርጓል


የኡጋንዳ ፕረዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ (Yoweri Museveni) ለብሩንዲ ሰላም ድርድር በተደረገ ስብሰባ ላይ በካምፓላ እንቴቤ ቤት [ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP]
የኡጋንዳ ፕረዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ (Yoweri Museveni) ለብሩንዲ ሰላም ድርድር በተደረገ ስብሰባ ላይ በካምፓላ እንቴቤ ቤት [ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP]

የቡሩንዲ ተቃዋሚዎች ጥምረት በሰላም ድርድሩ እንዲሳተፍ አልተጋበዝኩም በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በቡሩንዲ መንግስታና በተቃዋሚዎች መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር እንዲዘገይ ተደርጓል። መቼ እንደሚቀጠል አልተገለጸም።

ባለፈው ወር ኡጋንዳ የተጀምረው ንግግር ነገ በአሩሻ ታንዜንያ እንዲቀጥል ታቅዶ ነበር። ይሁንና “ግጭት የሚደግፉ ወገኖች” እንዲገቡበት ተደርጓል በሚል መንግስት በንግግሩ አልሳተፍም ሲል ትላንት ማስታወቁን ከፍተኛ የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ጆሴፍ ባንጉራምቦና (Joseph Bangurambona) ገልጸዋል።

የቡሩንዲ ተቃዋሚዎች ጥምረትም (CNARED) በንግግሩ እንዲሳተፍ አልተጋበዝኩም ብሏል።

የኡጋንዳ ፕረዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በቡሩንዲ ያለው የፖለቲካ ቀውስ እንዲያበቃ ለመሽምገል ጥረት እያደረጉ ናቸው። ቀውሱ የተነሳው ፕረዚዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ የስልጣን ጊዜ እንደሚወዳደሩ ባለፈው ሚያዝያ ወር ካስታወቁ በኋላ ነው።

ከዚያን ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ መዲና ቡጁምቡራ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ከ 400 በላይ የሚሆኑ ስዎች ተገድለዋል።

XS
SM
MD
LG