በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተነጋገሩ


በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል

​​ረዳት ሚኒስትር ማሊኖውስኪ ነገ ረቡዕና ሓሙስ ሩዋንዳን ይጎበኛሉ። በዚያ ከመንግስቱ ባለሥልጣናት እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ስለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ስለመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቁጥጥር ይነጋገራሉ። በአካባቢ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይትም የሚያካሂዱ መሆኑ ታውቋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።

ረዳት ሚኒስትር ማሊኖውስኪ ነገ ረቡዕና ሓሙስ ሩዋንዳን ይጎበኛሉ። በዚያ ከመንግስቱ ባለሥልጣናት እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ስለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ስለመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቁጥጥር ይነጋገራሉ። በአካባቢ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይትም የሚያካሂዱ መሆኑ ታውቋል።

ዓርብ ደግሞ ወደ ቡሩንዲ በማምራት የመንግስቱን ባለስልጣናት በሀገሪቱ ተፈጽሟል በተባለው የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ጉዳይ ባስቸኩዋይ ነጻ ምርመራ ማካሄድ አስፈላጊነት ይወያያሉ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ ከፊታችን ቅዳሜ አንስተው ረቡዕ ድረስ በኬንያ ጉብኝት ያደርጋሉ። በቆይታቸው ከመንግስት ባለሥልጣናት፣ ከጸጥታ ሃይሎች ሹማምንት፣ ከፓርላማ አባላት፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ተሙጋቾች፣ እንዲሆም ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ይወያያሉ።

ንቁና ጠንካራ የሲቪል ማኅበረሰብና፣ የህግ የበላይነትን አስፈላጊነት፣ በጸጥታ ጥበቃ ጥረቶች ወቅት ሰብዓዊ መብት ከበሬታና ጨምሮ ስፋት ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሚያነጋግሩዋቸው መሆኑን መግለጫው አውስቷል። በተጨማሪም በኬንያ መልካም አስተዳደርና ጸረ ሙስና ጥረቶችን ለማጎልበት በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተደረሰው የጋራ ስምምነት ተግባራዊነት ያለበትን ደረጃ በተመለከተም እንደሚነጋጋሩ ተመልክቷል።

እስክንድር ፍሬው የኢትዮጵያ ቆይታቸውን ተከታትሎ ከባልደረባችን ሰሎሞን አባተ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ አለ፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተነጋገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG