በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦኮ ሐራም ለአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቀምባቸው ልጆች ቁጥር እየጨመረ እንደሄደ የህጻናት መርጃ ድርጅት ገለጸ


ፋይል ፎቶ - ከቦኮ ሐራም ያመለጡ ህጻናት ልጆች በአዳማዋ ተብሎ የሚጠራ ሚችካ እና ካሜሮን ናይጄርያ መጠለያ እ.አ.አ.2015
ፋይል ፎቶ - ከቦኮ ሐራም ያመለጡ ህጻናት ልጆች በአዳማዋ ተብሎ የሚጠራ ሚችካ እና ካሜሮን ናይጄርያ መጠለያ እ.አ.አ.2015

የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ (UNICEF)የናይጀርያው ጽንፋኛ የአማጽያን ቡድን ለአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቀምባቸው ልጆች ቁጥር እየጨመረ እንደሄደ ገልጿል። ቡድኑ ለማጥቃት ተግባር ከሚጠቀሙባቸው ልጆች 75 ከመቶዎቹ ሴቶች እንደሆኑ ዩኒሴፍ ጠቁሟል።

ባለፈው አመት በናይጀርያ፣ በጎረቤት ሃገሮች ቻድ፣ ካሜሩናና ኒጀር በልጆች እንደተፈጸሙ የታወቁት የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች 44 መድረሳቸውን የህጽናት መርጃው ድርጅት ገልጿል። ሆኖም ቁጥሩ ከዚህ ይበዛል የሚል እምነት እንዳለው ድርጅት ጨምሮ አስገንዝቧል። ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት በአጥፍቶ ማጥፋት ተግባር ውስጥ የተሳተፉት ልጆች ብዛት በአስር እጥፍ እንደጨመረ ገልጿል። አቻ አመና የአጥፍቶ መጥፋት ተግባር የፈጸሙት ልጆች አራት ነበሩ ይላል ድርጅቱ።

የዩኒሴፍ (UNICEF) የምዕራብና የማዕከላዊ አፍሪቃ ክልላዊ ስራ አስኪያጅ ማኑየል ፎንተይን እነዚህ ልጆች በወንጀላኛነት ሳይሆን በሰለባነት ነው መታየት ያለባቸው ብለዋል።

“ብዙውን ጊዜ ቦምብ እንደተጠመደባቸው ሁሉ ላያውቁ ይችላሉ። በሌላው መልኩ ደግሞ ልጆች ስለሆኑ በሚነግሯቸው ነገሮች ታጥበው የሚፈጽሙት ተግባር ስለሚያስከትለው ነገር በትክክል ላይገነዘቡ ይችላሉ። ይህ ሁሉ ታድያ በልጆች ላይ ተፈጥሯዊ ያልሆነ የጥርጣሪ መንፈስ ያሳድራል።”ብለዋል።

ልጆችን በማታለል የግድያ ተግባር እንዲፈጽሙ ማስገደድ በናይጀርያና በጎረቤት ሀገሮች በሚካሄዱት ጥቃቶች ከአስከፊው ገጽታው አንዱ ነው ይላሉ ፎንተይን።

“በተጫማሪም በጣም የሚያሳስበን በተጠለፉት ልጆች፣ ጽንፈኛው ቡድን በተጠቀመባቸው፣ በአንዳንድ ሁኔታ ደግሞ በአማጽያኑ የወሲብ ጥቃት በተፈጸባቸውና ከነሱ በወለዱ ሴቶች እንዲሁም በአሸባሪው ቡድን በተመለመሉና መጠቀምያ በሆኑት ወንዶች ልጆች ላይ ያለው አመለካከት ነው። በአሉታዊ መልክ የመታየታቸው ጉዳይ እየጨመረ መሄዱን እያየን ነው።" ይላሉ።

ቦኮ ሃራም ለሁለት አመታት ከሚጠጋ ጊዜ በፊት ከ 200 በላይ የሚሆኑ ሴት ተማሪዎችን ቺቦክ ከሚገኘው ትምህርት ቤታቸው ከጠለፈበት ጊዜ ወዲህ በናይጀርያና በአጎራባች ሀገሮች ያለው የልጆች ሁኔታ እየተባባሰ እንደሄደ የህጻናት መርጃው ድርጅት ጠቁሟል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ሌሎች 2,000 የሚሆኑ ልጆች ከናይጀርያ፣ ከኒጀር፣ ከቻድና ከካሜሩን በቦኮ ሐራም እንደተጠለፉ ድርጅቱ አክሏል።

ከቦኮ ሃራም እገታ ነጻ የወጡ ሴቶች እንደሚሉት አማጽያኑ ለወሲብ ባርነት እንደሚጠቀሙባቸውና በወታደራዊ እንቃቃሴዎች እንዲረዱ እንደሚያስገድድዋቸው ገልጸዋል።

የናይጀርያና ክልላዊ ወታደራዊ ሃይሎች ተባብረው ካለፈው አመት ወዲህ ቦኮ ሐራምን ከከቶሞችና ከመንደሮች እየነቀሉ በመሆናቸው አማጽያኑ መቶ ወደ ማምለጥ ስትራቴጂ እንደተመለሱ ታውቋል።

ልጆች የሚሳተፉበት የአጥፍቶ ማጥፋት ተግባር እየተዘወተረ በመሆኑ ልጆች ለደህንነት አደጋ ተደርገው እየታዩ መሆናቸውን የዩኒሴፍ (UNICEF) የምዕራብና የማዕከላዊ አፍሪቃ ክልላዊ ስራ አስኪያጅ ማኑየል ፎንተይን ገልጸዋል። እንዲህ አይነቱ አመለካከት በጣም አሳሳቢ እንደሆነና የኑሮ ጊዜያቸውን መልሰው ለመገንባት በመጣር ላይ ላሉት ማኅበረሰቦች ጎጂ አንደምታ እንደሚኖረው ፎንተይን ጠቁመዋል።

ቦኮ ሐራም ለሰባት አመታታ ያህል ሲያካሄድ በቆየው የአመጽ እንቅስቃሴ 20,000 የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል። ከሁለት ሚልዮን በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ከመኖርያቸው አፈናቅሏል።

የቦኮ ሐራም አላማ በሰሜን ናይጀርያ በምዕራባውያን ትምህርት ላይ ጦርነት ማካሄድን ያካተት ጥብቅ እስላማዊ ህግ መደንገግ ነው።

ሂውማን ራይትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ቦኮ ሐራም በስድስት አመታት ውስጥ 611 አስተማሪዎችን ገድሏል ይላል። በትምህርት ቤቶች ላይ የሚካሄዱቱ ጥቃቶች ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችን አውድመዋል ወይም እንዲዘጉ አድርገዋል። በሰሜን ምስራቅ ናይጀርያ ወደ ሁለት ሚልዮን የሚጠጉ ልጆች የተምህርት ዕድል እንደተነፈጋቸው ሂውማን ራይትስ ዋች አስገንዝቧል።

ዘጋቢዎቻችን ሊዛ ሽላይን ከጄኔቫ እና ቺማ ንዋንክዎ ደግሞ ከአቡጃ ናይጄርያ የላክዋቸው ዘገባዎችን አጠናቅራ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ቦኮ ሐራም ለአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቀምባቸው ልጆች ቁጥር እየጨመረ እንደሄደ የህጽናት መርጃ ድርጅት ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG