በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ እንዲያፈነዱ የሚጠቀሙባቸው ልጆች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ዩኒሴፍ አስገነዘበ

በቦኮ ሃራም ምክኒያት የተፈናቀሉ ህጻናት በማይዲጉሪ ከተማ ናይጄርያ ውስጥ
በቦኮ ሃራም ምክኒያት የተፈናቀሉ ህጻናት በማይዲጉሪ ከተማ ናይጄርያ ውስጥ

ዩኒሴፍ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ባለፈው እ.አ. አ. 2015 ዓ. ም. አርባ አራት ልጆች በቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት መሳተፋቸውን ገልጾ ይህም ከዚያ በቀደመው ዓመት ከተሳተፉት አራት ልጆች ጋር ሲነጻጸር በአስር ዕጥፍ የሚበልጥ መሆኑን አመልክቷል።

የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ እንዲያፈነዱ የሚጠቀሙባቸው ልጆች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አስገነዘበ።

ዩኒሴፍ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ባለፈው እ.አ. አ. 2015 ዓ. ም. አርባ አራት ልጆች በቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት መሳተፋቸውን ገልጾ ይህም ከዚያ በቀደመው ዓመት ከተሳተፉት አራት ልጆች ጋር ሲነጻጸር በአስር ዕጥፍ የሚበልጥ መሆኑን አመልክቷል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተፈሙት የቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ከአምስቱ አንዱ ልጆች መሆናቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ ከልጆቹ መካከል ደግሞ ሰባ አምስት ከመቶው ልጃገረዶች መሆናቸውን አክሎ ገልጸዋል።

ረቤካ ኢሳቅ ከቦኮ ሃራም እጅ ካመለጡት የቺቦክ ሴቶች ልጆች አንዷ ናት
ረቤካ ኢሳቅ ከቦኮ ሃራም እጅ ካመለጡት የቺቦክ ሴቶች ልጆች አንዷ ናት

ሽብርተኛው ቡድን ልጆችን በአሸባሪነት ወደማይጠረጠሩባቸው ህዝብ የበዛባቸው ገበያዎችና መስጊዶች የመሳሰሉ አካባቢዎች ሲልኳቸው አንዳንዶቹ ቦምብ እንዳሲያዟቸው እንኳን ባላወቁበት መሆኑን ሪፖርቱ አውስቷል።

ዩኒሴፍ ሪፖርቱን ያወጣው ቦኮ ሃራም ከሰሜን ናይጄሪያዋ ቺቦክ ከተማ 276 ልጃገረዶችን የየጠለፈበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሲሆን ከመካከላቸው 219ኙ አሁንም አልተገኙም።

XS
SM
MD
LG