ዋሽንግተን ዲሲ —
ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ከማይድጉሪ ናይጀርያ ወጣ ብሎ በሚገኝ መስጊድ ላይ ባደረሱት ጥቃት 22 ሰዎች ሲገደሉ 17 ቆስለዋል።
አጥፍቶ ጠፊዎቹ የወንድ ልብስ የለበሱ ሴቶች እንደሆኑ የአይን ምስክሮች ተናግረዋል። አንደኛዋ ዛሬ ማለዳ መስጊድ ውስጥ ገብታ ፈንጂውን እንዳፈነዳች ሌላዋ ደግሞ ከመስጊዱ ውጭ ሆና አስቅድሞ ከፈንዳው ፈንጂ በሚሸሹት ሰዎች ላይ እንዳፈነዳች ተገልጿል።
ማይድጉሪ ቦኮ ሐራም የተባለው ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን አመጹን የጀመረበት ከተማ ተደርጋ ትታያለች። ቡድኑ በሰሜን ናይጀርያና በቻድ ባህር አከባቢ ባሉት ጎረቤት ሃገሮች ኒጀር፣ ቻድና ካሜሩን ጥቃቶች ሲያካሄድ ቆይቷል። የሀገሪቱ መንግስት ቡድኑን ለማጥፋት እየታገለ ነው። ለዛሬው ፍንዳታ እስካሁን ባለው ጊዜ ሃላፊነት የወሰደ የለም።