ዋሽንግተን ዲሲ —
የኬንያው መከላከያ ሠራዊት ሹም ሳምሶም ማዋቲቴ (Samson Mwathethe) እንዳስታወቁት፣ “ይህ ማለት ሁላችንም ወላጆች ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር ጋር በቅርብ መሥራትና ልጆቻችን ከአማጺው ቡድን ጋር እንዳያብሩ መከላከል እንደሚኖርብን አመላካች ነው።”
ጀነራሉ ይህን የተናገሩት፣ ትናንት ረቡዕ ናይሮቢ ውስጥ የኬንያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በተከበረበት ሥነ-ሥራት ላይ መሆኑም ታውቋል። ዕለቱ፣ ሶማልያ ውስጥ ከአል-ሻባብ ጋር በተካሄዱ ጦርነቶች ሕይወታችን የሰዉትን ሁሉ ለማስታወስ በመላ አገሪቱ የተከበረ እንደሆነም ተገልጧል።
የኬንያ ኃይሎች ሶማልያ የገቡት፣ እአአ በጥቅምት 2011 ሲሆን፣ እስከዛሬ ሶማልያ ያለውን የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የተቀላቀሉ የኬንያ መከላከያ ኃይሎች ቁጥር 4,000 መሆኑም ታውቋል።
በሌላ የሶማልያ ዜና፣ የናይጄሪያው አማጺ ቡድን ቦኮ ሀራም ለሶማልያው አል-ሻባብ የትብብር ጥያቄ ማቅረቡን ተሰማ። ነውጠኛው ቡድን ቦኮ ሀራም ለሶማልያው ሽምቅ ተዋጊ አል-ሻባብ ባቀረበው ጥሪ፣ አል-ቃዒዳን ትቶ እራሱን እስላማሚ መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ነውጠኛ ቡድን ጋር እንዲቀላቀል ጠይቋል።
አዲሱ አበበ ያቀረበውን ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።