በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪቃ እና የናይጄርያ መሪዎች በመካከላቸው ያለው ግንኙነት የሚጠናከርበት ሁናቴ ላይ እየመከሩ ነው


ሁለቱ መሪዎች፣ የጦር መሣሪያ ምርትን ጨምሮ፣ በተለያዩ የደኅንነት ትብብር ላይ መወያየታቸውንም የፕሬዚደንት ቡሃሪ የመገናኛ ብዙኃን ልዩ አማካሪ ጋርባ ሸሁ ገልጸዋል።

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ በናይጄሪያ የጀመሩትን የሦስት ቀናት ጉብኝታቸውን በመቀጠል፣ በሁለቱ የኤክኖሚ ባለጠጋ አገሮቻቸው መካከል ያለው ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁናቴ ላይ እየመከሩ መሆናቸው ተገለጸ።

የናይጄሪያው ፕሬዚደንት ቡሃሪ የመገናኛ ብዙኃን ልዩ አማካሪ ጋርባ ሸሁ በሰጡት መግለጫ፣ የፕሬዚደንት ዙማ ጉብኝት ለሁለቱም አገሮች እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አውስተው፣ በተለይም ናይጄሪያ ኢክኖሚዋን ከነዳጅ ምርት ወደ እርሻና ማዕድን የለወጠችበት ወቅት መሆኑንና እነዚህ ደግሞ ደቡብ አፍሪቃ በእጅጉ የምትተማመንባቸውና አመርቂ ዕድገት ያስመዘገበችባቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች መሆናቸውን አመልክተዋል።

ሁለቱ መሪዎች፣ የጦር መሣሪያ ምርትን ጨምሮ፣ በተለያዩ የደኅንነት ትብብር ላይ መወያየታቸውንም የፕሬዚደንት ቡሃሪ አማካሪ ጨምረው ገልጸዋል።

የሁለቱ አገሮች መሪዎች የአሁኑ ውይይት፣ ቀደም ሲል በሌላ የደኅንነት ጉዳይ ላይ ከነበራቸው አለመግባባት ቀጥሎ የተካሄደ መሆኑ ነው። ያም፣ የደቡብ አፍሪቃው ኤምቲኤን (MTN) የቴሌፎን ኩባንያ፣ አክራሪውን የቦኮ ሀራም ቡድን ይረዳል ሲሉ ፕሬዚደንት ቡሀሪ ትናንት ማክሰኞ መክሰሳቸው ነው።

"ምንም እንኳ ፕሬዚደንት ቡሃሪ በቀጥታ 'MTN ቦኮ ሀራምን ይረዳል' ብለው ክስ ባይመሰርቱም፣ ኩባንያው ግንያለ ሲም ካርድ(SIM Card) የሚገለገሉትንና ያልተመዘገቡትን ደምበኞቹን እንዲሰርዝ የቀረበለትን ጥያቄ አልፈጸመም" ሲሉ፣የናይጄሪያው ፕሬዚደንት ማካሪ ጋርባ ሸሁ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG