የናይጀርያ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሳኒ ኩካሼካ ኡስማን የናይጀርያ ወታደራዊ ሃይል በሀገሪቱ ዜጎች እየታገዘ ፕረዚዳንት ሙሐመዱ ቡሃሪ በጠየቁት መሰረት የያዝነው አመት በመጪው ታህሳሳ ወር ከማብቃቱ በፊት ቦኮ ሐራምን ለማዳከም ብቻ ሳይሆን ለማሸን ሌት ተቀን እየጣረ ነው ሲሉ ከባልደረባችን ጀምስ ባቲ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ተናግረዋል።
“አንዲት ሴት አጥፍቶ ጠፊ በወታደሮቻችንና በሌሎች የጸጥታ አገልግሎቶች በቦርኖ ክፍለ-ሃገር ከማይድጉሪ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የፍተሻ ቦታ ላይ ተጠለፈች። እንደተነቃባት ስታውቅ ታድያ በፍጥነት ፈንጂዎን አፈነዳችው። በጥቃቱም ስምንት ሰዎች ሲገደሉ ስምንት ቆስለዋል። አብዛኞቹም ሴቶችና ልጆች ናቸው።”
አጥፍቶ ጠፊዋ ከመኖርያቸው በተፈናቀሉ ሰዎች መሀል ሰርጋ የገባችው በተቻለ መጠን ብዙ
ሰዎችን ለመግደል ነበር ብለዋል ወታደራዊው ቃል አቀባይ ኮሎኒኣል ዑስማን።
“እስካሁን ባለው ጊዜ በተደረገው ምርመራ መሰረት አትፍቶ ጠፊዋ ከሌሎቹ ተፈናቃዮች ጋር ተቀላቅላ ምናልባትም ማይድጉሪ ከተማ ድረስ ዘልቃ የከፋ ጥፋት የመፈጸም አልማ እንደነበራት ለማወቅ ተችሏል።”
ቦኮ ሐራም ማይድጉሩ ላይ በርካታ የሽምቅ ውጊያ ይዘት ያላቸው ጥቃቶች ሲያካሄድ ቆይቷል። ይሁንና በከተማይቱ የሰዎችን ህይወት ለማትረፍና ንብረት ለመጠበቅ ሲባል በቂ የጸጥታ እርምጃዎች ተወስደዋል ብለዋል ኮሎኔል ዑስማን።
አያይዘውም ቃል አቀባዩ አሸባሪነትንና አመጽን መዋጋት ቀላል አይደለም። ይሁንና ማይድጉሪ በአሁኑ ጊዜ ተረጋግታለች ለማለት ይቻላል። በዛ እንደሚቀጥልም ተስፈ አደጋለሁ ብለዋል።
የቦኮ ሐራም መሪ አቡበከር ሽካኡ በቪድዮ ባስተላለፈው መልእክት ቡድኑ እስላማዊ መንግስት ነኝ ለሚለው ጽንፈኛ ቡድን ታማኝኑቱን እንደገለጸ አስታውቆ ነበር።
የናይጀርያ ወታደራዊው ሀይል ቦኮ አራም በፓሪስና በባማኮ የተፈጸሙትን ጥቅቶች አይነት እዚህ ይፈጽማል የሚል ስጋት የለውም። ቦኮ ሐራም መዳከም ብቻ ሳይሆን ይሸነፋል ሲሉ ቃል አቀባይ አስገንዝበዋል።
የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባችን ጀምስ ባቲ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቀርበዋለች። የድምጽ ፋይሉን ያዳምጡ።