በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐጅ በዓል የሞቱ የናይጄርያውያን ቁጥር ጨምሯል


በሐጅ በዓል የሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል
በሐጅ በዓል የሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

የናይጄርያ የሐጅ ኮሚሽን ባወጣው ዘገባ መሰረት፣ በሐጅ ከሞቱት ሰዎች መካከል 74 ናይጄርያውያን ሲሆኑ 64 ደግሞ ቆስለዋል። የዜና ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ከሰሀራ በመለስ ካሉት፣ የአፍሪቃ ሀገሮች መካከል፣ ብዙ ምዕመናን የሞቱባት ናይጄርያ ናት።

የናይጄርያ የሐጅ ኮሚሽን ባወጣው ዘገባ መሰረት፣ በሐጅ ከሞቱት ሰዎች መካከል 74 ናይጄርያውያን ሲሆኑ 64 ደግሞ ቆስለዋል። የዜና ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ከሰሀራ በመለስ ካሉት፣ የአፍሪቃ ሀገሮች መካከል፣ ብዙ ምዕመናን የሞቱባት ናይጄርያ ናት።

የሙታኑ ብዛት ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል። ወደ ሐጅ ከተጓዙት ናይጄርያውያን 244 የሚሆኑት፣ እስካሁን ባለው ጊዜ፣ የገቡበት አልታወቀም። የሀገሪቱ የሐጅ ኮሚሽን ፍለጋ እያካሄደ ነው። የናይጄርያ ህዝብ ከሞላ ጎደል እኩል፣ በክርስትያኖችና በሙስሊሞች መካከል የተከፋፈለ ሲሆን፣ በያዝነው አመት ወደ ሓጅ የተጓዙት፣ 85,000 እንደሚሆኑ ኮሚሽኑ ገልጿል።

ብዙዎቹ የሰሜናዊትዋ ከተማ ካዱና ነዋሪዎች፣ ከሞቱት መከከል ዘመድ ወይም ወዳጅ ያላቸው ናቸው። ዩሱፍ ያኩቡ አርጋሲዩ የተባሉት፣ የናይጀርያ የሙስሊም ተጠያቂነት ማህብር ዋና ስራ-አስኪያጅ፣ ከሞቱት መካከል ብዙዎቹን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

የናይጄርያው ክሪስ ስተይን (Chris Stein) እና ኢብራሂም ያኩቡ (Ibrahim Yakubu) ከናይጄርያ የላኩትን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቀናብራ አቅርባዋለች።

ሙሉውን ዘገባ የድምፅ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

በሐጅ በዓል የሞቱ የናይጄርያውያን ቁጥር ጨምሯል /ርዝመት - 2ደ55ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG